ዘኍል 3:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታቦቱንም፥ ገበታውንም፥ መቅረዙንም፥ መሠዊያዎቹንም፥ ካህናቱም የሚገለገሉባቸውን የመቅደሱን ዕቃዎች፥ መጋረጃውንም፥ መገልገያውንም ሁሉ ይጠብቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ታቦቱን፣ ጠረጴዛውን፣ መቅረዙን፣ መሠዊያዎቹን፣ ለመቅደሱ አገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች፣ መጋረጃዎችንና ከነዚህ ጋራ ተያይዞ አገልግሎት የሚሰጠውን ሁሉ ይጠብቃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእነርሱም ኀላፊነት በቃል ኪዳኑ ታቦት፥ በገበታው፥ በመቅረዙ፥ በመሠዊያዎቹ፥ ካህናቱ በተቀደሰው ስፍራ በሚገለገሉባቸው ንዋያተ ቅድሳት፥ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን በሚያስገባው መጋረጃ ላይ ሲሆን፥ በአጠቃላይ እነዚህን ነገሮች በሚመለከት አገልግሎት ኀላፊነቱ የእነርሱ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታቦቱንም፥ ገበታውንም፥ መቅረዙንም፥ መሠዊያዎቹንም፥ የሚያገለግሉበትንም የመቅደሱን ዕቃ፥ መጋረጃውንም፥ ማገልገያውንም ሁሉ ይጠብቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታቦቱንም፥ ገበታውንም፥ መቅረዙንም፥ መሠዊያዎቹንም፥ የሚያገለግሉበትንም የመቅደሱን ዕቃ፥ መጋረጃውንም፥ ማገልገያውንም ሁሉ ይጠብቃሉ። |
በዚያን ጊዜ የጌታን ቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከም፥ እርሱንም ለማገልገል በጌታ ፊት እንዲቆም፥ በስሙም እንዲባርክ ጌታ እስከ ዛሬ ድረስ የሌዊን ነገድ ለየ።