Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 3:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 የሌዋውያንም አለቆች አለቃ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ይሆናል፤ እርሱም የመቅደሱን ግዴታ በሚፈጽሙት ላይ ተቆጣጣሪ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ዋናው የሌዋውያን አለቃ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ነው፤ እርሱም መቅደሱን ለመጠበቅ ኀላፊ በሆኑት ላይ ተሹሞ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 የሌዋውያን ሁሉ አለቃ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ነበር፤ እርሱ በተቀደሰው ስፍራ ለሚያገለግሉት ሰዎች ሁሉ የበላይ ኀላፊ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 የሌ​ዋ​ው​ያ​ንም አለ​ቆች አለቃ የተ​ቀ​ደሱ ነገ​ሮ​ችን ይጠ​ብቅ ዘንድ የተ​ሾ​መው የካ​ህኑ የአ​ሮን ልጅ አል​ዓ​ዛር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 የሌዋውያንም አለቆች አለቃ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ይሆናል፤ እርሱም መቅደሱን በሚጠብቁት ላይ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 3:32
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሠራዊቱ አዛዥ ናቡዛርዳን ሊቀ ካህናቱን ሤራያን በማዕረግ የእርሱ ምክትል የሆነውን ካህኑን ሶፎንያስና ሦስቱን የቤተ መቅደስ ዘበኞች እስረኛ አድርጎ ወሰዳቸው፤


የአቢሹዓ ልጅ፥ የፊንሐስ ልጅ፥ የኤልዓዛር ልጅ፥ የታላቁ ካህን የአሮን ልጅ፥


እንዲህም አለኝ፦ “ይህ ወደ ደቡብ የሚመለከት ቤት ቤቱን ለሚጠብቁ ካህናት ነው፥


ታቦቱንም፥ ገበታውንም፥ መቅረዙንም፥ መሠዊያዎቹንም፥ ካህናቱም የሚገለገሉባቸውን የመቅደሱን ዕቃዎች፥ መጋረጃውንም፥ መገልገያውንም ሁሉ ይጠብቃሉ።


በሜራሪ ውስጥ የሞሖላውያን ወገንና የሙሳያውያን ወገን ይካተቱ ነበር፤ የሜራሪ ወገኖች እነዚህ ናቸው።


“የካህኑም የአሮን ልጅ አልዓዛር በመብራቱ ዘይት መዓዛውም በሚያምር ዕጣን ላይ፥ ሁልጊዜም በሚቀርበው በእህሉ ቁርባንና በቅባቱ ዘይት ላይ ይሾም፤ ማደሪያውን ሁሉ፥ በእርሱም ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ መቅደሱንና ዕቃውን ይቆጣጠር።”


የጌድሶናውያን አገልግሎት ሁሉ፥ ሸክማቸውም ሁሉ፥ ሥራቸውም ሁሉ በአሮንና በልጆቹ ትእዛዝ ይሁን፤ በየአገልግሎታቸውም የሚደርስባቸውን ሸክም ሁሉ ለእያንዳንዳቸው ትደለድላላችሁ።


በየወገኖቻቸውም በየአባቶቻቸውም ቤቶች የተቈጠሩት ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሠላሳ ነበሩ።


ወንድሞቻቸው የተሰጣቸውን ግዴታ እንዲወጡ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይርዱአቸው እንጂ የድንኳኑን አገልግሎት አይሠሩ። በየአገልግሎታቸው በመደልደል በሌዋውያን ላይ እንዲሁ ታደርጋለህ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች