ዘኍል 3:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሮን ልጆች፥ እርሱም በክህነት አገልግሎት እንዲያገለግሉ የቀደሳቸው፥ የተቀቡ ካህናት ስሞቻቸው እነዚህ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ለክህነት አገልግሎት የለያቸው፣ ካህናት ለመሆን የተቀቡት የአሮን ወንድ ልጆች ስም ይህ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህም በክህነት እንዲያገለግሉ ተቀብተው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በክህነት ያገለግሉ ዘንድ የተቀቡና እጆቻቸውን የተቀደሱ የአሮን ልጆች ስም ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተቀቡ ካህናት በክህነትም ያገለግሉ ዘንድ የቀደሳቸው የአሮን ልጆች ስም ይህ ነው። |
ወንድምህን አሮንንና ከእርሱም ጋር ልጆቹን እነዚህን አልብሳቸው፤ በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀባቸዋለህ፥ እጆቻቸውንም ታነጻለህ፥ ትቀድሳቸዋለህም።
ሙሴም ከቅባቱ ዘይትና በመሠዊያው ላይ ካለው ከደሙ ወስዶ በአሮንና በልብሱ ላይ፥ በልጆቹና በልጆቹ ልብስ ላይ ረጨው፤አሮንንና ልብሱንም፥ ልጆቹንም፥ የልጆቹንም ልብስ ቀደሰ።
ናዳብና አብዩድ በሲና ምድረ በዳ በጌታ ፊት ያልተፈቀደውን እሳት ባቀረቡ ጊዜ በጌታ ፊት ሞቱ፤ ልጆችም አልነበሩአቸውም። አልዓዛርና ኢታምር በአባታቸው በአሮን ፊት በክህነት ያገለግሉ ነበር።