ዘፀአት 40:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 አባታቸውን እንደ ቀባህ ትቀባቸዋለህ፥ ካህናትም ይሆኑልኛል፤ ቅባታቸውም ለሚመጣው ትውልድ ሁሉ ለዘለዓለም ክህነት ይሆንላቸዋል።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ካህናት ሆነው ያገለግሉኝ ዘንድ ልክ አባታቸውን እንደ ቀባህ ቅባቸው፤ መቀባታቸውም በሚመጡት ትውልዶች ሁሉ ለሚቀጥል ክህነት ነው።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 እነርሱም ካህናት ሆነው ያገለግሉኝ ዘንድ ልክ አባታቸውን በቀባኸው ዐይነት ቀባቸው፤ በመቀባታቸውም ምክንያት በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ካህናት ሆነው ያገለግሉኛል።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 አባታቸውን እንደ ቀባህ ትቀባቸዋለህ፤ ካህናትም ይሆኑኛል። ይህም ለልጅ ልጃቸው ለዘለዓለም የክህነት ቅብዐት ይሆንላቸዋል።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 በክህነትም ያገለግሉኝ ዘንድ አባታቸውን እንደ ቀባህ ትቀባቸዋለህ፤ መቀባታቸውም ለልጅ ልጃቸው ለዘላለም ክህነት ይሆንላቸዋል። ምዕራፉን ተመልከት |