ዘኍል 21:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ በጌታ የጦርነት መጽሐፍ እንዲህ ተባለ፦ “ዋሄብ በሱፋ፥ የአርኖንም ሸለቆች፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ በእግዚአብሔር የጦርነት መጽሐፍ እንዲህ ተብሎ የተጻፈው በዚሁ የተነሣ ነው፤ “…በሱፋ ውስጥ የሚገኘው ዋሄብ አርኖንና አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም የተነሣ በእግዚአብሔር መሪነት ስለ ተደረገው ጦርነት በሚናገር የታሪክ መጽሐፍ እንዲህ ተብሎአል፦ “በሱፋ ክልልና በሸለቆዎች ውስጥ የሚገኘው ዋሄብ፥ የአርኖን ወንዝ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ በመጽሐፍ ተባለ የእግዚአብሔር ጦርነት ዞኦብንና የአርኖን ሸለቆዎችን አቃጠለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በእግዚአብሔር የጦርነት መጽሐፍ እንዲህ ተባለ፦ ዋሄብ በሱፋ፥ የአርኖንም ሸለቆች፥ |
ከዚያም ተጉዘው ከአሞራውያን ዳርቻ ትይዩ በተዘረጋው ምድረ በዳ ውስጥ በአርኖን ማዶ ሰፈሩ፤ አርኖን በሞዓብና በአሞራውያን መካከል ያለ የሞዓብ ዳርቻ ነውና።
“ደግሞም አለ፦ ‘ተነሥታችሁ ሂዱ፥ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ፥ እነሆ፥ አሞራዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንን ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ እርሷን በመውረስ ጀምር፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ።
ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመች፥ ጨረቃም ዘገየች። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ጸንታ ቆመች፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለችም።
ሳኦል ዳዊትን፥ “ታላቋ ልጄ ሜራብ እነኋት፤ እርሷን እድርልሃለሁ፤ አንተ ግን በጀግንነት አገልግለኝ፤ የጌታንም ጦርነቶች ተዋጋልኝ” አለው፤ ሳኦል በልቡ፥ “ፍልስጥኤማውያን እጃቸውን ያንሡበት እንጂ እኔ በእርሱ ላይ እጄን አላነሣም” ብሎ ነበር።