ኢያሱ 10:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመች፥ ጨረቃም ዘገየች። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ጸንታ ቆመች፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለችም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ስለዚህ ሕዝቡ ጠላቶቹን እስኪበቀል ድረስ፣ ፀሓይ ባለችበት ቆመች፤ ጨረቃም አልተንቀሳቀሰችም። ይህም በያሻር መጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል። ፀሓይ በሰማዩ መካከል ቆመች፤ ለመጥለቅም ሙሉ ቀን ፈጀባት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፤ ጨረቃም ካለችበት ሳትንቀሳቀስ ቈየች፤ ይህም በያሻር መጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል። ሳይንቀሳቀስ በሰማይ መካከል ቆመ፤ ቀኑንም ሙሉ ሳይጠልቅ ቈየ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 እግዚአብሔርም ጠላቶቻቸውን እስኪያጠፋ ድረስ ፀሐይና ጨረቃ በየቦታቸው ቆሙ። ይህም እነሆ በዚህ መጽሐፍ በጊዜው ተጻፈ። ፀሐይም በሰማይ መካከል ቆመች፤ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል አልጠለቀችም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም። ምዕራፉን ተመልከት |