Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 21:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ከዚያም ተጉዘው ከአሞራውያን ዳርቻ ትይዩ በተዘረጋው ምድረ በዳ ውስጥ በአርኖን ማዶ ሰፈሩ፤ አርኖን በሞዓብና በአሞራውያን መካከል ያለ የሞዓብ ዳርቻ ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከዚያም ተነሥተው እስከ አሞራውያን ግዛት በሚዘልቀው ምድረ በዳ ባለው በአርኖን አጠገብ ሰፈሩ፤ አርኖን በሞዓብና በአሞራውያን መካከል የሚገኝ የሞዓብ ወሰን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከዚያም ተጒዘው እስከ አሞራውያን ግዛት በሚዘልቀው ምድረ በዳ ከአርኖን ወንዝ ማዶ በሚገኘው ቦታ ሰፈሩ፤ የአርኖን ወንዝ በሞአባውያንና በዐሞራውያን ግዛት ወሰን ላይ የሚገኝ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ከዚ​ያም ተጕ​ዘው ከአ​ሞ​ራ​ው​ያን ዳርቻ በሚ​ወ​ጣው ምድረ በዳ ውስጥ በአ​ር​ኖን ማዶ ሰፈሩ፤ አር​ኖን በሞ​ዓ​ብና በአ​ሞ​ራ​ው​ያን መካ​ከል ያለ የሞ​ዓብ ዳርቻ ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ከዚያም ተጕዘው ከአሞራውያን ዳርቻ በሚወጣው ምድረ በዳ ውስጥ በአርኖን ማዶ ሰፈሩ፤ አርኖን በሞዓብና በአሞራውያን መካከል ያለ የሞዓብ ዳርቻ ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 21:13
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ቀጥሎም የኤዶምንና የሞዓብን ምድር በመዞር፥ በምድረ በዳው ተጉዞ ከሞዓብ በስተ ምሥራቅ በኩል በማለፍ ከአርኖን ማዶ ሰፈረ፤ የሞዓብም ድንበር አርኖን ስለ ነበር ወደ ሞዓብ ክልል አልገባም።


ባላቅም በለዓም እንደመጣ በሰማ ጊዜ በአርኖን ድንበር በድንበሩም ጨረሻ ወዳለችው ወደ ሞዓብ ከተማ ሊገናኘው ወጣ።


ሞዓብም ፈርሶአልና አፈረ፤ አልቅሱ ጩኹም፤ ሞዓብ እንደ ጠፋ በአርኖን አጠገብ አውጁ።


ከጎጆቸው ተበትነው እንደሚበሩ ወፎች፥ የሞዓብ ሴቶችም በአርኖን መሻገሪያዎች እንዲሁ ይሆናሉ።


“ደግሞም አለ፦ ‘ተነሥታችሁ ሂዱ፥ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ፥ እነሆ፥ አሞራዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንን ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ እርሷን በመውረስ ጀምር፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ።


ስለዚህ በጌታ የጦርነት መጽሐፍ እንዲህ ተባለ፦ “ዋሄብ በሱፋ፥ የአርኖንም ሸለቆች፥


“አሁንም፥ ‘ተነሡ የዘሬድንም ፈፋ ተሻገሩ፤’ አለን። የዘሬድንም ፈፋ ተሻገርን።


‘አንተ ዛሬ የሞዓብን ዳርቻ ዔርን ታልፋለህ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች