እያንዳንዱ ካህን ከሚያገለግላቸው ሰዎች የሚገኘውን የገንዘብ መባ ሁሉ በጥንቃቄ የመጠበቅ ኃላፊነት ተሰጠው፤ ገንዘቡንም እንዳስፈላጊነቱ ለቤተ መቅደሱ ጥገና አገልግሎት እንዲያውሉት ነገራቸው።
ዘኍል 18:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታ ከሚያቀርቡት ከሰው ወይም ከእንስሳ ማናቸውም ማኅፀን የሚከፍት ሥጋ ለባሽ የሆነ ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን በኵራት ፈጽሞ ትዋጀዋለህ፥ ያልነጻውንም እንስሳ በኵራት ትዋጀዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማሕፀን የሚከፍትና ለእግዚአብሔር የተሰጠ ሰውም ሆነ እንስሳ የአንተ ነው፤ ነገር ግን ማንኛውም በኵር ሆኖ የተወለደውን ወንድ ልጅና ንጹሕ ካልሆነ እንስሳ በኵር ሆኖ የተወለደውን ተባዕት ሁሉ ዋጀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስራኤላውያን ለእኔ የሚያቀርቡት የሰውም ሆነ የእንስሳ በኲር ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን የበኲር ልጅ ለመዋጀት ዋጋውን በጥሬ ገንዘብ መቀበል አለባችሁ፤ እንዲሁም ንጹሕ ስላልሆነው የእንስሳ በኲር ምትክ ዋጋውን በጥሬ ገንዘብ መቀበል ትችላላችሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰው እስከ እንስሳ ቢሆን፥ ለእግዚአብሔር ከሚያቀርቡት ሥጋ ሁሉ፥ መጀመሪያ የሚወለድ ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን በኵራት ፈጽሞ ትቤዠዋለህ፤ ያልነጹትንም እንስሳት በኵራት ትቤዣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔር ከሚያቀርቡት ሥጋ ሁሉ ማኅፀን የሚከፍት ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን በኵራት ፈጽሞ ትቤዠዋለህ፥ ያልነጻውንም እንስሳ በኵራት ትቤዠዋለህ። |
እያንዳንዱ ካህን ከሚያገለግላቸው ሰዎች የሚገኘውን የገንዘብ መባ ሁሉ በጥንቃቄ የመጠበቅ ኃላፊነት ተሰጠው፤ ገንዘቡንም እንዳስፈላጊነቱ ለቤተ መቅደሱ ጥገና አገልግሎት እንዲያውሉት ነገራቸው።
የእህላችንንም በኵራት፥ የእጅ ማንሣታችንን ቁርባን፥ የዛፍ ሁሉ ፍሬ፥ ወይኑንና ዘይቱንም ወደ ካህናቱ ወደ አምላካችን ቤት ጓዳዎች እናመጣ ዘንድ፥ ሌዋውያኑም ከከተሞቻችን እርሻ ሁሉ አሥራት ይቀበላሉና የመሬታችንን አሥራት ወደ ሌዋውያን እናመጣ ዘንድ ማልን።
ፈርዖን እንዳይለቀን ልቡን ባጸና ጊዜ ጌታ ከሰው በኩር ጀምሮ እስከ እንስሳ በኩር ድረስ በግብጽ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ ገደለ፤ ስለዚህ ወንድ ሆኖ ማሕፀንን የከፈተውን ሁሉ ለጌታ እሠዋለሁ፥ ነገር ግን የልጆቼን በኩር ሁሉ እዋጃለሁ።
የአህያውን በኩር በጠቦት ትዋጀዋለህ፥ ካልዋጀኸው ግን አንገቱን ትሰብረዋለህ። የልጆችህንም በኩር ሁሉ ትዋጃለህ። በፊቴ አንድ ሰው ባዶ እጁን አይታይ።
ከአንድ ወር ጀምሮ የምትዋጀውን እንደ ግምትህ ትዋጀዋለህ፤ ግምቱም እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን አምስት ሰቅል ይሆናል፤ እርሱም ሀያ አቦሊ ነው።
ምክንያቱም በኩር ሁሉ የእኔ ነውና፤ በግብጽ ምድር በኩርን ሁሉ በገደልሁ ቀን፥ ከእስራኤል ዘንድ በኩርን ሁሉ፥ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ያለውን ለእኔ ለይቼአለሁ፤ ለእኔ ይሆናሉ። እኔ ጌታ ነኝ።”
“የቀንድ ከብት፥ የበግና የፍየል መንጋዎችህን ተባዕት በኩር ሁሉ ለጌታ ለእግዚአብሔር ትቀድሳለህ። የበሬህን በኩር አትሥራበት፤ የበግህንም በኩር አትሸልት፤