ነህምያ 10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)የፈረሙ ሰዎች ዝርዝር 1 በዚህም ሁሉ የታመነውን ቃል ኪዳን አድርገን እንጽፋለን፤ መሪዎቻችን፥ ሌዋውያኖቻችንና ካህናቶቻችን ያትሙበታል። 2 ያተሙትም እነዚህ ናቸው፤ የሐካልያ ልጅ ገዢው ነህምያ፥ ጺድቂያ፥ 3 ሠራያ፥ አዛርያ፥ ኤርምያስ፥ 4 ፓሽሑር፥ አማርያ፥ ማልኪያ፥ 5 ሐጡሽ፥ ሽባንያ፥ ማሉክ፥ 6 ሐሪም፥ ምሬሞት፥ አብድዩ፥ 7 ዳንኤል፥ ጊንቶን፥ ባሩክ 8 ሜሹላም፥ አቢያ፥ ሚያሚን፥ 9 ማዓዝያ፥ ቢልጋይ፥ ሽማዕያ፤ እነዚህ ካህናት ነበሩ። 10 ሌዋውያኑ ደግሞ፦ የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፥ ከሔናዳድ ልጆች ቢኑይ፥ ቃድሜል፥ 11 ወንድሞቻቸው ሽባንያ፥ ሆዲያ፥ ቅሊጣ፥ ፕላያ፥ ሐናን፥ 12 ሚካ፥ ርሖብ፥ ሐሻብያ፥ 13 ዛኩር፥ ሼሬብያ፥ ሽባንያ፥ 14 ሆዲያ፥ ባኒ፥ ብኒኑ። 15 የሕዝቡ መሪዎች፦ ፓርዖሽ፥ ፓሓት ሞዓብ፥ ዔላም፥ ዛቱ፥ ባኒ፥ 16 ቡኒ፥ ዓዝጋድ፥ ቤባይ፥ 17 አዶኒያ፥ ቢግዋይ፥ ዓዲን፥ 18 አጤር፥ ሕዝቅያስ፥ ዓዙር፥ 19 ሆዲያ፥ ሐሹም፥ ቤጻይ፥ 20 ሐሪፍ፥ ዓናቶት፥ ኖባይ፥ 21 ማግፒዓሽ፥ ምሹላም ሔዚር፥ 22 ምሼዛብኤል፥ ጻዶቅ፥ ያዱዓ፥ 23 ፕላጥያ፥ ሐናን፥ ዓናያ፥ 24 ሆሴዕ፥ ሐናንያ፥ ሓሹብ፥ 25 ሃሎሔሽ፥ ፒልሐ፥ ሾቤቅ፥ 26 ርሁም፥ ሐሻብና፥ ማዓስያ 27 አሒያ፥ ሐናን፥ ዓናን፥ 28 ማሉክ፥ ሐሪም፥ ባዓና። የቃል ኪዳኑ ማጠቃለያ 29 የቀሩት ሕዝብ፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ በር ጠባቂዎቹ፥ መዘምራን፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች፥ ከምድር ሕዝቦች ወደ እግዚአብሔር ሕግ ራሳቸውን የለዩ ሁሉ፥ ሚስቶቻቸው፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው፥ የሚያውቁትና የሚያስተውሉት ሁሉ፥ 30 ከወንድሞቻቸውና ከመኳንንቶቻቸው ጋር በመሆን በእግዚአብሔር ባርያ በሙሴ እጅ በተሰጠው በእግዚአብሔር ሕግ ለመሄድ፥ የጌታ አምላካችንን ትእዛዞቹን ሁሉ፥ ፍርዶቹንና ሥርዓቶቹን ለመጠበቅና ለማድረግ ወደ እርግማንና መሐላ ገቡ። 31 ሴቶች ልጆቻችንን ለምድሪቱ ሕዝቦች አንሰጥም፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችን አንወስድም፤ 32 የምድሪቱ ሕዝቦች ሸቀጥ ወይም ልዩ ልዩ እህል ለመሸጥ በሰንበት ቀን ቢያመጡ፥ በሰንበት ወይም በተቀደሰ ቀን ከእነርሱ አንገዛም፤ በሰባተኛው ዓመትም ምድሪቱን እናሳርፋታለን፥ ዕዳንም ሁሉ እንሰርዛለን። 33 ለአምላካችን ቤት አገልግሎት የሚውል አንድ ሦስተኛ ሰቅል በየዓመቱ ለመስጠት በራሳችን ላይ ትእዛዝ እናስቀምጣለን። ስለ ገጸ ኅብስትም፥ ዘወትርም በሰንበትና በመባቻ ስለ ማቅረብ ስለ እህሉ ቁርባንና ስለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ስለ በዓላትም፥ ስለ ተቀደሱትም ነገሮች፥ ለእስራኤልም ስለሚያስተሰርየው ስለ ኃጢአት መሥዋዕት፥ ስለ አምላካችንም ቤት ሥራ ሁሉ በየዓመቱ የሰቅል ሢሶ እናመጣ ዘንድ ትእዛዝ በራሳችን ላይ አደረግን። 34 እኛም፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ ሕዝቡም፥ እንደ አባቶቻችን ቤቶች በተወሰነ ጊዜ በየዓመቱ ወደ አምላካችን ቤት አምጥተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይቃጠል ዘንድ ስለ እንጨት ቁርባን ዕጣ ተጣጣልን፥ 35 በየዓመቱም የመሬታችንን በኵራት የሁሉ ዓይነት ዛፍ የፍሬ ሁሉ በኵራት ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣ ዘንድ፥ 36 በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት፥ በአምላካችን ቤት ወደ ሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥ 37 የእህላችንንም በኵራት፥ የእጅ ማንሣታችንን ቁርባን፥ የዛፍ ሁሉ ፍሬ፥ ወይኑንና ዘይቱንም ወደ ካህናቱ ወደ አምላካችን ቤት ጓዳዎች እናመጣ ዘንድ፥ ሌዋውያኑም ከከተሞቻችን እርሻ ሁሉ አሥራት ይቀበላሉና የመሬታችንን አሥራት ወደ ሌዋውያን እናመጣ ዘንድ ማልን። 38 ሌዋውያኑም አሥራቱን በተቀበሉ ጊዜ የአሮን ልጅ ካህኑ ከሌዋውያን ጋር ይሁን፥ ሌዋውያኑም የአሥራቱን አሥራት ወደ አምላካችን ቤት ወደ ጓዳዎች ወደ ዕቃ ቤት ያምጡት። 39 የእስራኤል ልጆችና የሌዊ ልጆችም የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም የማንሣት ቁርባንን የመቅደሱ ዕቃዎችና የሚያገለግሉት ካህናት በረኞቹና መዘምራኑ ወዳሉባቸው ጓዳዎች ያግቡት፥ እንዲሁም የአምላካችንን ቤት ከቶ አንተውም። |