Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 13:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ፈርዖን እንዳይለቀን ልቡን ባጸና ጊዜ ጌታ ከሰው በኩር ጀምሮ እስከ እንስሳ በኩር ድረስ በግብጽ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ ገደለ፤ ስለዚህ ወንድ ሆኖ ማሕፀንን የከፈተውን ሁሉ ለጌታ እሠዋለሁ፥ ነገር ግን የልጆቼን በኩር ሁሉ እዋጃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ፈርዖን እኛን አልለቅም ብሎ ልቡን ባደነደነ ጊዜ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ በኵር ሆኖ በግብጽ የተወለደውን ሁሉ እግዚአብሔር ገደለው። እንግዲህ በመጀመሪያ የእናቱን ማሕፀን የከፈተውን ወንድ ሁሉ ለእግዚአብሔር የምሠዋውና የልጆቼ በኵር ሆኖ የተወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ የምዋጀው በዚህ ምክንያት ነው።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የግብጽ ንጉሥ ልቡን አደንድኖ እልኸኛ በመሆን አለቃችሁም ባለ ጊዜ እግዚአብሔር በግብጽ ምድር የሰውንም ሆነ የእንስሶችን በኲር ሁሉ ገደለ፤ በኲር ሆኖ የተወለደውን ወንድ እንስሳ መሥዋዕት አድርጌ የማቀርበው በዚህ ምክንያት ነው፤ በኲር ሆነው የተወለዱትን ወንዶች ልጆቻችንን ግን እንዋጃቸዋለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ፈር​ዖ​ንም እኛን ለመ​ል​ቀቅ እንቢ ባለ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰው በኵር ጀምሮ እስከ እን​ስሳ በኵር ድረስ በግ​ብፅ ምድር ያለ​ውን በኵር ሁሉ ገደለ፤ ስለ​ዚህ ወንድ ሆኖ ማሕ​ፀ​ንን የከ​ፈ​ተ​ውን ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሠ​ዋ​ለሁ፤ ነገር ግን የል​ጆ​ችን በኵር ሁሉ እዋ​ጃ​ለሁ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ፈርዖንም እንዳይሰድደን ልቡን ባጸና ጊዜ እግዚአብሔር ከሰው በኵር ጀምሮ እስከ እንስሳ በኵር ድረስ በግብፅ ምድር ያለውን በኵር ሁሉ ገደለ፤ ስለዚህ ወንድ ሆኖ ማሕፀንን የከፈተውን ሁሉ ለእግዚአብሔር እሠዋለሁ፤ ነገር ግን የልጆቼን በኵር ሁሉ እዋጃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 13:15
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲህም ሆነ እኩለ ሌሊት ላይ ጌታ በግብጽ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ፥ በዙፋን ከተቀመጠው ከፈርዖን በኩር ጀምሮ በእስር ቤት እስካሉት እስከ እስረኞች በኩር ድረስ፥ የከብቶችንም በኩር ሁሉ መታ።


የአህያውን በኩር በጠቦት ትዋጀዋለህ፥ ካልዋጀኸው ግን አንገቱን ትሰብረዋለህ። የልጆችህንም በኩር ሁሉ ትዋጃለህ። በፊቴ አንድ ሰው ባዶ እጁን አይታይ።


ከሌዋውያን ወንዶች ቍጥር በላይ የሆኑትን ሁለት መቶ ሰባ ሦስት የእስራኤል ልጆች በኵራትን ለመዋጀት፥


ለጌታ ከሚያቀርቡት ከሰው ወይም ከእንስሳ ማናቸውም ማኅፀን የሚከፍት ሥጋ ለባሽ የሆነ ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን በኵራት ፈጽሞ ትዋጀዋለህ፥ ያልነጻውንም እንስሳ በኵራት ትዋጀዋለህ።


የአገራቸውንም በኩር ሁሉ፥ የጉልበታቸውን መጀመሪያ ሁሉ መታ።


ነገር ግን በጽኑ እጅ ካልሆነ በቀር የግብጽ ንጉሥ እንድትሄዱ እንደማይፈቅድላችሁ እኔ አውቃለሁ።


እንዲያገለግለኝ ልጄን ልቀቅ አልሁህ፤ አንተም ትለቅቀው ዘንድ እንቢ አልህ፤ እነሆ እኔ የበኩር ልጅህን እገድላለሁ።’”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች