ዘኍል 16:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተን ከአንተም ጋር የሌዊን ልጆች ወንድሞችህን ሁሉ ወደ እርሱ እንድትቀርቡ ፈቅዶላችኋል፤ ታዲያ አሁን ደግሞ ክህነትንም ትፈልጋላችሁን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተንና ከአንተም ጋራ ወገኖችህ የሆኑትን ሌዋውያንን ሁሉ ወደ ራሱ አቅርቧችኋል፤ እናንተ ግን የክህነቱንም ሥራ ደርባችሁ ለመያዝ ይኸው ትሯሯጣላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ እናንተና ሌሎቹም ሌዋውያን ይህ ክብር እንዲኖራችሁ አድርጎአል፤ አሁን ደግሞ የካህናቱን ቦታ ለመያዝ ፈልጋችኋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተን ከአንተም ጋር የሌዊን ልጆች ወንድሞችህን ሁሉ ወደ እርሱ አቅርቦአል፤ ካህናትም ትሆኑ ዘንድ ትፈልጋላችሁን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተን ከአንተም ጋር የሌዊን ልጆች ወንድሞችህን ሁሉ ወደ እርሱ አቅርቦአል፤ ክህነትንም ደግሞ ትፈልጋላችሁን? |
ጌታም አሮንን እንዲህ አለው፦ “አንተ ከአንተም ጋር ልጆችህና የአባቶችህ ቤት ከመቅደሱ ጋር በተገናኘ የሚፈጸምን በደል ትሸከማላችሁ፤ አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ ከክህነታችሁ ጋር በተገናኘ የሚፈጸምን በደል ትሸከማላችሁ።
አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ ለመሠዊያው የሚደረገውን ነገር ሁሉ፥ በመጋረጃውም ውስጥ የሚሆነውን እንድታደርጉ የክህነታችሁን ግዴታዎች በትጋት ፈጽሙ፥ አገልግሉም፤ ክህነታችሁን እንደ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁ፤ ሌላም ሰው ቢቀርብ ይገደል።”
ከራስ ወዳድነት ወይም ከትምክሕት የተነሣ አንድም ነገር አታድርጉ፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው በትሕትና ባልንጀራውን ከራሱ ይልቅ እንደሚሻል አድርጎ ይቁጠር፤