Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 13:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በትዕቢት ጠብ ብቻ ይሆናል፥ ጥበብ ግን ምክርን በሚቀበሉ ዘንድ ናት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ትዕቢት ጠብን ብቻ ያስፋፋል፤ ጥበብ ግን ምክርን በሚቀበሉ ዘንድ ትገኛለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ትዕቢት ጠብን ያመጣል፤ ምክርን መጠየቅ ግን ብልኅነት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ክፉ ሰው ከመሳደብ ጋር ክፋትን ይሠራል፤ ራሳቸውን የሚያውቁ ግን ብልሆች ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 13:10
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝቡ፥ ንጉሥ ሮብዓም ጥያቄውን እንዳልተቀበለው በተገነዘበ ጊዜ “ከዳዊት ጋር ምን ድርሻ አለን? ከእሴይ ልጅ ከዳዊት ጋር ምን ርስት አለን፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ወደየድኳንኖችህ ሂድ! ዳዊት ሆይ የራስህን ቤት ጠብቅ!” ብለው መለሱለት። ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ ወደየቤቱ ሄደ።


አሜስያስ ሆይ! እነሆ፥ አንተም ኤዶማውያንን ድል ስላደረግህ ልብህ በትዕቢት ተሞልቶአል፤ በአገኘኸውም ድል በመደሰት ዐርፈህ በቤትህ ብትቀመጥ ይሻልሃል፤ በአንተና በሕዝብህ ላይ መቅሠፍትን የሚያስከትል ነገር ለመቆስቆስ ስለምን ትፈልጋለህ?”


በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፥ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች።


ሁልጊዜ ለጻድቃን ብርሃን ነው፥ የኀጥኣን መብራት ግን ይጠፋል።


የጠብ መጀመሪያ እንደ ውኃ አፈሳሰስ ነው፥ ስለዚህ ጠብ ሳይበረታ አንተ ክርክርን ተው።


ምክርን ስማ፥ ተግሣጽንም ተቀበል በፍጻሜህ ጠቢብ ትሆን ዘንድ።


አሳብ በምክር ትጸናለች፥ በመልካምም ምክር ሰልፍ አድርግ።


ኩሩና ተጓዳጅ ሰው ፌዘኛ ይባላል፥ እርሱም በትዕቢት ቁጣ ያደርጋል።


ባልንጀራህ ባሳፈረህ ጊዜ ኋላ እንዳትጸጸት ለሙግት ወደ ሽንጎ ፈጥነህ አትውጣ፥


ስግብግብ ሰው ክርክርን ያነሣሣል፥ በጌታ የሚታመን ግን ይጠግባል።


ደግሞም ከእነሱ መሀል ማን እንደሚበልጥ ለማወቅ ክርክር ተነሣ።


በትዕቢት የተወጠረና ምንም የማያውቅ ነው፤ ነገር ግን የንትርክና በቃላት የመከራከር ለየት ያለ ክፉ ምኞት አለበት፤ እነዚህም ነገሮች የሚያመጡት ቅንዓትን፥ መከፋፈልን፥ ስድብን፥ ክፉ ጥርጣሬን፥


በእናንተ መካከል ያለው ጦርነትና ጠብ ከየት የመጣ ነው? በውስጣችሁ ከሚዋጋው ከፍትወት ምኞት አይደለምን?


ያየም ሁሉ፥ “እስራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ ጀምሮ እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አልታየም፤ አልተደረገም፤ ምን ማድረግ እንዳለብንም በነገሩ አስቡበት፤ ተመካከሩ በት” ተባባሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች