Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 16:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አን​ተን ከአ​ን​ተም ጋር የሌ​ዊን ልጆች ወን​ድ​ሞ​ች​ህን ሁሉ ወደ እርሱ አቅ​ር​ቦ​አል፤ ካህ​ና​ትም ትሆኑ ዘንድ ትፈ​ል​ጋ​ላ​ች​ሁን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 አንተንና ከአንተም ጋራ ወገኖችህ የሆኑትን ሌዋውያንን ሁሉ ወደ ራሱ አቅርቧችኋል፤ እናንተ ግን የክህነቱንም ሥራ ደርባችሁ ለመያዝ ይኸው ትሯሯጣላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አንተን ከአንተም ጋር የሌዊን ልጆች ወንድሞችህን ሁሉ ወደ እርሱ እንድትቀርቡ ፈቅዶላችኋል፤ ታዲያ አሁን ደግሞ ክህነትንም ትፈልጋላችሁን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እርሱ እናንተና ሌሎቹም ሌዋውያን ይህ ክብር እንዲኖራችሁ አድርጎአል፤ አሁን ደግሞ የካህናቱን ቦታ ለመያዝ ፈልጋችኋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አንተን ከአንተም ጋር የሌዊን ልጆች ወንድሞችህን ሁሉ ወደ እርሱ አቅርቦአል፤ ክህነትንም ደግሞ ትፈልጋላችሁን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 16:10
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ ቤተ ክርስቲያን ጻፍሁ፤ ዳሩ ግን ዋናቸው ሊሆን የሚወድ ዲዮጥራፊስ አይቀበለንም።


በክ​ር​ክ​ርና ከንቱ ውዳ​ሴን በመ​ው​ደድ አት​ሥሩ፤ ትሕ​ት​ናን በያዘ ልቡና ከራ​ሳ​ችሁ ይልቅ ባል​ን​ጀ​ራ​ች​ሁን አክ​ብሩ እንጂ አት​ታ​በዩ።


እርስ በር​ሳ​ችሁ በወ​ን​ድ​ማ​ማ​ች​ነት መዋ​ደድ ተዋ​ደዱ፤ የም​ት​ራ​ሩም ሁኑ፤ እርስ በር​ሳ​ችሁ ተከ​ባ​በሩ፤ መም​ህ​ሮ​ቻ​ች​ሁ​ንም አክ​ብሩ።


ከዚ​ህም በኋላ ከእ​ነ​ርሱ ማን እን​ደ​ሚ​በ​ልጥ እርስ በር​ሳ​ቸው ተከ​ራ​ከሩ።


ክፉ ሰው ከመሳደብ ጋር ክፋትን ይሠራል፤ ራሳቸውን የሚያውቁ ግን ብልሆች ናቸው።


አን​ተም ከአ​ን​ተም ጋር ልጆ​ችህ እንደ መሠ​ዊ​ያ​ውና፥ በመ​ጋ​ረ​ጃ​ውም ውስጥ እን​ዳ​ለው ሥር​ዐት ሁሉ ክህ​ነ​ታ​ች​ሁን ጠብቁ፤ የሀ​ብተ ክህ​ነት አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ች​ሁ​ንም አድ​ርጉ፤ ከሌ​ላም ወገን የሆነ ሰው ቢቀ​ርብ ይገ​ደል።”


አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት አቁ​ማ​ቸው፤ ክህ​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም፥ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውና በመ​ጋ​ረ​ጃው ውስጥ ያለ​ው​ንም ሁሉ ይጠ​ብቁ፤ ከሌላ ወገን የዳ​ሰሰ ቢኖር ይገ​ደል።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “አንተ ከአ​ን​ተም ጋር ልጆ​ች​ህና የአ​ባ​ቶ​ችህ ወገ​ኖች፥ የክ​ህ​ነ​ታ​ች​ሁን ኀጢ​አት ትሸ​ከ​ማ​ላ​ችሁ።


ሚካም ሌዋ​ዊ​ዉን እጁን ቀባው፤ ጐል​ማ​ሳ​ውም ካህን ሆነ​ለት፤ በሚ​ካም ቤት ኖረ።


“የሌ​ዊን ነገድ አቅ​ር​በህ ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ በካ​ህኑ በአ​ሮን ፊት አቁ​ማ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች