Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 18:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጌታም አሮንን እንዲህ አለው፦ “አንተ ከአንተም ጋር ልጆችህና የአባቶችህ ቤት ከመቅደሱ ጋር በተገናኘ የሚፈጸምን በደል ትሸከማላችሁ፤ አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ ከክህነታችሁ ጋር በተገናኘ የሚፈጸምን በደል ትሸከማላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር አሮንን እንዲህ አለው፤ “መቅደሱን በተመለከተ ስለሚፈጸም በደል አንተ፣ ልጆችህና የአባትህ ቤተ ሰቦች ኀላፊነቱን ትሸከማላችሁ፤ ክህነቱን በተመለከተ ስለሚፈጸም በደል ግን ኀላፊነቱ የሚወድቀው በአንተና በልጆችህ ላይ ብቻ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር አሮንን እንዲህ አለው፤ “በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በሚከናወነው አገልግሎት ስለሚፈጸመው በደል ሁሉ አንተና ልጆችህ፥ ሌዋውያንም ኀላፊነቱን ትሸከማላችሁ፤ በክህነት አገልግሎት ለሚፈጸመው በደል ግን ኀላፊነቱን የምትሸከሙት በተለይ አንተና ልጆችህ ብቻ ናችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “አንተ ከአ​ን​ተም ጋር ልጆ​ች​ህና የአ​ባ​ቶ​ችህ ወገ​ኖች፥ የክ​ህ​ነ​ታ​ች​ሁን ኀጢ​አት ትሸ​ከ​ማ​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እግዚአብሔርም አሮንን አለው፦ አንተ ከአንተም ጋር ልጆችህና የአባቶችህ ቤት የመቅደስን ኃጢአት ትሸከማላችሁ፤ አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ የክህነታችሁን ኃጢአት ትሸከማላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 18:1
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በአሮን ግምባር ላይ ይሆናል፥ አሮንም የእስራኤል ልጆች በሚያቀርቡትና በሚቀድሱት በቅዱስ ስጦታቸው ሁሉ ላይ ያለውን ኃጢአት ይሸከም፤ በጌታ ፊት ሞገስ እንዲሆንላቸው ቅጠሉ ሁልጊዜ በግምባሩ ላይ ይሁን።


ከነፍሱ ሥቃይ ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ አገልጋዬ በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፤ ኃጢአታቸውንም ይሸከማል።


እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ ጌታም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።


አንተም በግራ ጐንህ ተኛ፥ የእስራኤልንም ቤት ኃጢአት አኑርባት፥ በምትተኛበትም ቀኖች ቍጥር ኃጢአታቸውን ትሸከማለህ።


“እጅግ የተቀደሰ ነውና፥ የሕዝቡንም ኃጢአት እንድትሸከሙ፥ በጌታም ፊት እንድታስተሰርዩላቸው ለእናንተ ሰጥቶአልና ለምን የኃጢአት መሥዋዕት የሆነውን በቅዱሱ ስፍራ አልበላችሁም?


ከዚህም የተነሣ የምቀድሳቸው እኔ ጌታ ነኝና የእነርሱን የተቀደሰ ነገር በሚበሉበት ጊዜ ኃጢአትንና በደልን እንዳይሸከሙ ነው።”


ባረክሱት ጊዜ እንዳይሞቱ ስለ እርሱም ኃጢአትን እንዳይሸከሙ፥ ትዛዝን ይጠብቁ፤ የምቀድሳቸው እኔ ጌታ ነኝ።


ምድሪቱን በሰላለችሁባት ቀን ቍጥር፥ አርባ ቀን፥ እያንዳንዱም ቀን እንደ አንድ ዓመት ሆኖ፥ በደላችሁን አርባ ዓመት ትሸከማላችሁ፥ መከፋቴንም ታውቃላችሁ።’


አንተን ከአንተም ጋር የሌዊን ልጆች ወንድሞችህን ሁሉ ወደ እርሱ እንድትቀርቡ ፈቅዶላችኋል፤ ታዲያ አሁን ደግሞ ክህነትንም ትፈልጋላችሁን?


ፈጽሞ ወደ ጌታ ማደሪያ የሚቀርብ ሁሉ፥ ይሞታል፤ በውኑ ሁላችን እንሞታለንን?”


በሌዊም በትር ላይ የአሮንን ስም ጻፍ። ለእያንዳንዱ ለአባቶቻቸው ቤት አለቃ አንድ በትር ይኖራቸዋልና።


ሙሴም በትሮቹን በጌታ ፊት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ አኖራቸው።


ይህም ደግሞ ለአንተ ነው፤ የእስራኤል ልጆች ለስጦታ የሚያቀርቡትን የመወዝወዝ ቁርባን ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ድርሻ እንዲሆን ለዘለዓለም ሰጥቼሃለሁ፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው።


“የሌዊን ነገድ አምጥተህ አቅርብ እንዲያገለግሉትም በካህኑ በአሮን ፊት አቁማቸው።


በዚያን ጊዜ የጌታን ቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከም፥ እርሱንም ለማገልገል በጌታ ፊት እንዲቆም፥ በስሙም እንዲባርክ ጌታ እስከ ዛሬ ድረስ የሌዊን ነገድ ለየ።


ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም። እነርሱ እንደሚጠየቁበት አድርገው ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ፤ ይህንንም በደስታ እንጂ በኀዘን እንዳያደርጉት፥ አለበለዚያ አይጠቅማችሁም።


እኛ ያለን ሊቀ ካህናት በድካማችን ሊራራልን የሚችል ነው፤ እርሱ በሁሉ ነገር እንደ እኛ ተፈተነ፤ ሆኖም ምንም ኃጢአት አልሠራም።


ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቁስል እናንተ ተፈውሳችኋል።


ሚካም ሌዋዊውን ካህን አድርጎ አስቀመጠው፤ ወጣቱም ካህኑ ሆነ፤ በቤቱም ኖረ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች