ዘኍል 15:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ነገር ግን ስሕተት ባለማወቅ ብትፈጽሙ፥ ጌታም ለሙሴ ያዘዛቸውን እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ ባታደርጉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘እንግዲህ ካለማወቅ የተነሣ እግዚአብሔር ለሙሴ ከሰጣቸው ትእዛዞች አንዱን ሳትፈጽሙ ብትቀሩ፣ ይህም ማለት አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ምናልባት እናንተ ሆን ብላችሁ ሳይሆን ባለማወቅ እግዚአብሔር ለሙሴ ከሰጠው ትእዛዞች መካከል አንዱን ሳትጠብቁ ብትቀሩ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ብትበድሉም፥ እግዚአብሔር ለሙሴ ያዘዛቸውን እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ ባታደርጉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብትስቱም፥ እግዚአብሔርም ለሙሴ ያዘዛቸውን እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ ባታደርጉ፥ |
ካህኑም ከእነዚያ በአንዳቸው ስለ ሠራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል። እንደ እህል ቁርባንም እንዲሁ የተረፈው ለካህኑ ይሆናል።”
ያላወቀ ግን መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ጥቂት ይገረፋል። ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፤ ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ አብዝተው ይሹበታል።