ዘኍል 1:49 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሌዊን ነገድ ብቻ አትቁጠረው፥ የሕዝብ ቈጠራ ስታደርግ እነርሱን ከእስራኤል ልጆች ጋር አትቁጠር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሌዊን ነገድ አትቍጠር፤ በእስራኤላውያንም ቈጠራ ውስጥ አታስገባው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስራኤላውያን ወንዶችን ስትቈጥር፥ የሌዊን ነገድ አትጨምር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሌዊን ነገድ እንዳትቈጥራቸው፥ ቍጥራቸውንም ከእስራኤል ልጆች ጋር እንዳትቀበል ዕወቅ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍጥራቸውንም ከእስራኤል ልጆች ጋር አታድርግ፤ |
ዕድሜአቸው አንድ ወር የሞላቸውና ከዚያም በላይ ያሉት ወንዶች ሁሉ ከእነርሱ የተቈጠሩ ሀያ ሦስት ሺህ ነበሩ። ከእስራኤልም ልጆች መካከል ርስት አልተሰጣቸውምና ከእስራኤል ልጆች ጋር አልተቈጠሩም።