ዕዝራ በእግዚአብሔር ቤት ፊት በግንባሩ ወድቆ እያለቀሰ በሚጸልይበትና በሚናዘዝበት ጊዜ፤ ወንዶች፥ ሴቶችና ሕፃናት የሚገኙበት እጅግ ታላቅ ጉባኤ ወደ እርሱ ተሰበሰበ፥ ሕዝቡም እጅግ አለቀሱ።
ነህምያ 13:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጅግም አስከፋኝ፥ የጦብያንም የቤቱን ዕቃ ሁሉ ከጓዳ ወደ ውጪ ጣልሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም በጣም ዐዘንሁ፤ የጦቢያንም የቤት ዕቃ ሁሉ ከክፍሉ እያወጣሁ ወደ ውጭ ጣልሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቊጣ ተነሥቼ የጦቢያን ንብረት ሁሉ ከክፍሉ በማስወጣት አሽቀንጥሬ ጣልኩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጅግም አስከፋኝ፤ የጦብያንም የቤቱን ዕቃ ሁሉ ከዕቃ ቤት ወደ ውጭ ጣልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጅግም አስከፋኝ፥ የጦብያንም የቤቱን ዕቃ ሁሉ ከጓዳ ወደ ውጪ ጣልሁ። |
ዕዝራ በእግዚአብሔር ቤት ፊት በግንባሩ ወድቆ እያለቀሰ በሚጸልይበትና በሚናዘዝበት ጊዜ፤ ወንዶች፥ ሴቶችና ሕፃናት የሚገኙበት እጅግ ታላቅ ጉባኤ ወደ እርሱ ተሰበሰበ፥ ሕዝቡም እጅግ አለቀሱ።