ማቴዎስ 20:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ጌታ ሹሙን ‘ሠራተኞቹን ጥራና ኋላ ከመጡት ጀምረህ መጀመሪያ እስከመጡት ድረስ ደመወዝ ስጣቸው፤’ አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ባለቤት የሠራተኞቹን ተቈጣጣሪ፣ ‘ኋላ ከመጡት ጀምረህ መጀመሪያ እስከመጡት ድረስ ያሉትን ሠራተኞች በሙሉ ጥራና ደመወዛቸውን ክፈላቸው’ አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ባለቤት የሥራ ኀላፊውን ‘ሠራተኞቹን ጥራና በመጨረሻ ከተቀጠሩት ጀምረህ በፊት እስከ ተቀጠሩት ድረስ የሥራ ዋጋቸውን ክፈላቸው’ አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ጌታ አዛዡን ‘ሠራተኞችን ጥራና ከኋለኞች ጀምረህ እስከ ፊተኞች ድረስ ደመወዝ ስጣቸው፤’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ጌታ አዛዡን፦ ሠራተኞችን ጥራና ከኋለኞች ጀምረህ እስከ ፊተኞች ድረስ ደመወዝ ስጣቸው አለው። |
ኤጲስ ቆጶስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ ነቀፋ የሌለበት ሊሆን ይገባዋል፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ ጠበኛ ያልሆነ፥ ለገንዘብ የማይስገበገብ፥
እንዲሁም ክርስቶስ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ተሰውቷል። ለሁለተኛ ጊዜ ሲታይ ሊያድናቸው ለሚጠባበቁት ኃጢአትን ለመሸከም ሳይሆን መዳንን ለማምጣት ነው።