Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 19:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “በባልንጀራህ ግፍ አታድርግ፥ አትቀማውም። ተቀጥሮ የሚያገለግለውን ሰው ደመወዙን እስከ ነገ ድረስ በአንተ ዘንድ አታቆይበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ ‘ባልንጀራህን አታጭበርብር፤ አትቀማውም። “ ‘የሙያተኛውን ደመወዝ ሳትከፍል አታሳድር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “በጐረቤትህ ላይ ግፍ አትሥራ፤ ወይም ንብረቱን አትቀማው፤ ቀጥረህ የምታሠራውን ሰው ደመወዝ ለአንድ ሌሊት እንኳ በአንተ ዘንድ አይደር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 “በባ​ል​ን​ጀ​ራህ ግፍ አታ​ድ​ርግ፤ አት​ቀ​ማ​ውም። የሞ​ያ​ተ​ኛው ዋጋ እስከ ነገ ድረስ በአ​ንተ ዘንድ አይ​ደ​ር​ብህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በባልንጀራህ ግፍ አታድርግ፥ አትቀማውም። የሞያተኛው ዋጋ እስከ ነገ ድረስ በአንተ ዘንድ አይደርብህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 19:13
29 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለብዝበዛ ባልንጀሮቹን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው፥ የልጆቹ ዐይን ይጨልማል።”


ፍሬዋን ያለ ዋጋ በልቼ፥ የባለቤቶችንም ነፍስ አሳዝኜ እንደሆነ፥


አገልጋይ ጥላ እንደሚመኝ፥ ምንደኛም ደመወዙን እንደሚጠብቅ፥


አንድ ሰው ከባልንጀራው አንዳች ቢዋስ ባለቤቱም ከእርሱ ጋር ሳይኖር ቢጎዳ፥ ወይም ቢሞት፥ ካሳ ይክፈለው።


“ሰው ያልታጨችውን ድንግል ቢያታልላት፥ ከእርሷም ጋር ቢተኛ፥ የማጫዋን ዋጋ ሰጥቶ ሚስት ያድርጋት።


መበለቲቱንና ድሀ አደጉን አታስጨንቁአቸው።


ሌባው ግን ባይገኝ፥ እጁን በባልንጀራው ንብረት ላይ እንዳልዘረጋ እንዲታወቅ ባለቤቱ ወደ እግዚአብሔር ፊት ይቅረብ።


ሁለት ዓይነት ሚዛንና ሁለት ዓይነት መስፈሪያ፥ ሁለቱ በጌታ ፊት ርኩሳን ናቸው።


ድሀን አትግፈፈው ድሀ ነውና፥ ችግረኛውንም በበር አትጨቁነው፥


በጎ ነገርን ማድረግ ሲቻልህ፥ ወዳጅህን፦ “ሂድና ተመለስ፥ ነገ እሰጥሃለሁ” አትበለው።


“ቤቱን በግፍ ሰገነቱንም በዓመፅ ለሚሠራ፥ ባልንጀራውንም እንዲያው በከንቱ ለሚያሠራ፥ ዋጋውንም ለማይሰጠው፤


ጌታ እንዲህ ይላል፦ ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ የተበዘበዘውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ፤ መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም አትበድሉ፥ አታምፁባቸውም፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ።


ማንንም ሰው ባያስጨንቅ፥ ነገር ግን ለባለ ዕዳው መያዣውን ቢመልስ፥ ባይቀማ፥ ከምግቡ ለተራበ ቢሰጥ፥ የተራቆተውንም በልብስ ቢሸፍን፥


ደም ለማፍሰስ በአንቺ ውስጥ ጉቦን ተቀበሉ፥ አንቺም አራጣና ትርፍ ወስደሻል፥ ጎረቤቶችሽንም ጨቁነሽ የማይገባ ትርፍ አገኘሽ፥ እኔንም ረሳሽኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


የምድሪቱ ሕዝብ ግፍ አደረጉ፥ ዝርፊያም ፈፀሙ፥ ድሃውንና ችግረኛውን አንገላቱ፥ መጻተኛውንም ያለ ፍትሕ በደሉ።


ለባልንጀራህም መሬት ብትሸጥ፥ ወይም ከባልንጀራህ እጅ ብትገዛ፥ አንዱ ሌላውን አያታልል።


እኔም ጌታ አምላካችሁ ነኝና ሰው ባልንጀራውን አያታልል፥ ነገር ግን አምላክህን ፍራ።


ወይም የጠፋውን ነገር ቢያገኝ፥ ያንንም ሸሽጎ በሐሰት ቢምል፥ ሰው ከሚያደርጋቸው ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች ኃጢአት በአንዱ ቢሠራ፥


ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት በሚምሉ፥ የሠራተኛውን ደመወዝ በሚያስቀሩ፥ መበለቲቱንና የሙት ልጅን በሚያስጨንቁ፥ ስደተኛውን በሚገፉ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ጌታ ሹሙን ‘ሠራተኞቹን ጥራና ኋላ ከመጡት ጀምረህ መጀመሪያ እስከመጡት ድረስ ደመወዝ ስጣቸው፤’ አለው።


ትእዛዛትን ታውቃለህ፤ አትግደል፤ አታመንዝር፤ አትስረቅ፤ በሐሰት አትመስክር፤ አታታልል፤ አባትህንና እናትህን አክብር።”


እርሱም፦ “ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ ምንም አትሰብስቡ፤” አላቸው።


አስቀድመን ደግሞ እንደ ነገርናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።


ቅዱስ መጽሐፍ፦ “የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር፤” ደግሞ “ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል፤” ይላል።


እነሆ፥ እርሻችሁን ሲያጭዱ ለዋሉ ሠራተኞች ያልከፈላችሁት ደመወዝ በእናንተ ላይ ይጮኻል፤ የአጫጆቹም ጩኸት የሠራዊት ጌታ ጆሮ ደርሶአል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች