ማቴዎስ 15:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቱን አያከብርም”’ ስለ ልማዳችሁም ስትሉ የእግዚአብሔርን ቃል ሻራችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘አንድ ሰው ይህን ካደረገ አባቱን ወይም እናቱን አክብሯል’ ትላላችሁ። ስለዚህ ለወጋችሁ ብላችሁ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ያ ሰው አባቱን [ወይም እናቱን] ማክበር አያስፈልገውም’ ትላላችሁ፤ ስለዚህ ወጋችሁን ለማጥበቅ ብላችሁ የእግዚአብሔርን ሕግ ታፈርሳላችሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቱን ወይም እናቱን አያከብርም፤” ትላላችሁ፤’ ስለ ወጋችሁም የእግዚአብሔርን ቃል ሻራችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቱን ወይም እናቱን አያከብርም ትላላችሁ፤ ስለ ወጋችሁም የእግዚአብሔርን ቃል ሻራችሁ። |
ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ትተሃልና ለእኔ ካህን እንዳትሆን ትቼሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።
አማኝ የሆነች ማንም ሴት መበለታት ዘመዶች ቢኖሩአት፥ እነርሱን ትርዳቸው፤ ቤተክርስትያንም በእርግጥ እርዳታ የሚያሻቸውን መበለታትን መርዳት እንድትችል ሸክም አይሁኑባት።