Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 8:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 “እናንተስ፦ ‘ጥበበኞች ነን የጌታንም ሕግ ከእኛ ጋር ነው’ እንዴት ትላላችሁ? እነሆ፥ በውኑ የጸሐፊዎች ሐሰተኛ ብዕር ሐሰት አድርጎታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ ‘የጸሓፊዎቻችሁ ሐሰተኛ ብርዕ ሐሰት እያስተናገደ እንዴት፣ “ዐዋቂዎች ነን፣ የእግዚአብሔር ሕግ አለን” ትላላችሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ታዲያ ‘እኛ ጠቢባን ነን፤ የእግዚአብሔርንም ሕግ እናውቃለን’ የምትሉት ስለምንድን ነው? ሐሰተኞች ጸሐፊዎች ሕጌን እንዳዛቡ አትመለከቱምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 “እና​ን​ተስ፦ ጥበ​በ​ኞች ነን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ ከእኛ ጋር ነው እን​ዴት ትላ​ላ​ችሁ? እነሆ ጸሓ​ፊ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ከንቱ ሆኑ፤ በሐ​ሰ​ትም ብርዕ ተጠ​ቀሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እናንተስ፦ ጥበበኞች ነን የእግዚአብሔርም ሕግ ከእኛ ጋር ነው እንዴት ትላላችሁ? እነሆ፥ የጸሐፊ ብርዕ ሐሰተኛ ነው በሐሰትም አድርጎአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 8:8
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሜዳ አህያ ሰው ሆኖ ሲወለድ፥ ከንቱ ሰው ጥበብን ያገኛል።”


ከታመኑ ሰዎችም ቋንቋን ያርቃል፥ የሽማግሌዎችንም ማስተዋል ይወስድባቸዋል።


ቃሉን ለያዕቆብ፥ ሥርዓቱንና ፍርዱን ለእስራኤል ይናገራል።


የሽማግሌዎች አክሊል የልጅ ልጆች ናቸው፥ የልጆችም ክብር አባቶቻቸው ናቸው።


ፊተኛው አባትህ ኃጢአት ሠርቶአል፥ መምህሮችህም በድለውኛል።


እነርሱም፦ “ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፥ በኤርምያስ ላይ ሤራን እናሢር። ኑ፥ በአንደበት እንምታው፥ ቃላቱንም ሁሉ አናድምጥ” አሉ።


በዚህም ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምክር አፈርሳለሁ፥ በጠላቶቻቸውም ፊት በሰይፍና ነፍሳቸውን በሚሹት እጅ እጥላቸዋለሁ፥ ሬሳቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል አድርጌ እሰጣለሁ።


ካህናቱም፦ ‘ጌታ ወዴት አለ?’ አላሉም፥ የሕግ አዋቂዎች አላወቁኝም፤ ገዢዎችም ዐመፁብኝ፥ ነቢያትም በበዓል ትንቢት ተናገሩ፥ የማይረባውንም ነገር ተከተሉ።


“ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም፤ ሰነፎች ልጆች ናቸው፥ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፥ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።”


እናንተ፦ እኛ ኃያላን በውጊያም ጽኑዓን ነን፥ እንዴት ትላላችሁ?


በሺዎች የሚቆጠሩትን ሕጎቼን ጽፌለት እንኳ እንደ እንግዳ ነገር ተቆጠሩ።


አባቱን አያከብርም”’ ስለ ልማዳችሁም ስትሉ የእግዚአብሔርን ቃል ሻራችሁ።


ኢየሱስም አላቸው “ዕውሮችስ ብትሆኑ ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባችሁ ነበር፤ አሁን ግን ‘እናያለን’ ትላላችሁ፤ ኀጢአታችሁም በዚያው ይኖራል።


ጥበበኞች ነን ሲሉ ሞኞች ሆኑ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች