139 ጠላቶቼ ቃልህን ረስተዋልና የቤትህ ቅንዓት አቀለጠኝ።
139 ጠላቶቼ ቃልህን ዘንግተዋልና፣ ቅናት አሳረረኝ።
139 ጠላቶቼ ትእዛዞችህን አለመቀበላቸው በጣም ያበሳጨኛል።
ደቀ መዛሙርቱም “የቤትህ ቅንዓት ይበላኛል፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ አሰቡ።
ለወንድሞቼ እንደ ሌላ፥ ለእናቴ ልጆችም እንደ እንግዳ ሆንሁባቸው።
በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችና አለቆቻቸው እርሱንና በየሰንበቱ የሚነበቡትን የነቢያትን ድምፆች ስላላወቁ በፍርዳቸው ፈጽመዋልና፤
ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔንም እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ!” ሲል መለሰ።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው “ስታችኋል፥ ምክንያቱም መጻሕፍትን ወይም የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና።
ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፤’ የሚለውን ከቶ በመጽሕፍት አላነበባችሁምን?
“እነዚህ የሚሉትን ትሰማለህን?” አሉት። ኢየሱስም “አዎን እሰማለሁ፤ ‘ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ’ የሚለውን ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው።
“‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል’ ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የዘራፊዎች ዋሻ አደረጋችሁት” አላቸው።
ሂዱና ‘ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤’ የሚለው ምን እንደሆነ ተማሩ፤ ኃጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና፤”
ሁሉም በደሉ፥ አብረውም ረከሱ፥ አንድ እንኳ በጎን ነገር የሚያደርጋት የለም።
ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔን እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ” ሲል መለሰ።
የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና፥ የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና።