ኢዩም፦ ጓደኞቹ ወደ ሆኑት ወደ ጦር መኰንኖቹ በመጣ ጊዜ “ሁሉ ነገር ሰላም ነውን? ለመሆኑ ይህ እብድ ከአንተ ምን ይፈልጋል?” ሲሉ ጠየቁት። ኢዩም “ሰውየውንም ሆነ እርሱ የሚናገረውን እናንተ ታውቁታላችሁ” አላቸው።
ማቴዎስ 11:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፤ እነርሱም ‘ጋኔን አለበት’ አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሐንስ ከመብልና ከመጠጥ ተቈጥቦ በመምጣቱ፣ ‘ጋኔን አለበት’ ይሉታልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም መጥምቁ ዮሐንስ በመጣ ጊዜ እህል ሳይበላና የወይን ጠጅ ሳይጠጣ ቢመጣ፥ ‘ይህስ ጋኔን አለበት!’ አሉት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፤ እነርሱም ‘ጋኔን አለበት’ አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፥ እነርሱም፦ ጋኔን አለበት አሉት። |
ኢዩም፦ ጓደኞቹ ወደ ሆኑት ወደ ጦር መኰንኖቹ በመጣ ጊዜ “ሁሉ ነገር ሰላም ነውን? ለመሆኑ ይህ እብድ ከአንተ ምን ይፈልጋል?” ሲሉ ጠየቁት። ኢዩም “ሰውየውንም ሆነ እርሱ የሚናገረውን እናንተ ታውቁታላችሁ” አላቸው።
‘በጌታ ቤት አለቃ ሆነህ እያበደ ትንቢት የሚናገርን ሰው ሁሉ በመንቈርና በዛንጅር አስረህ እንድታኖረው ጌታ በካህኑ በዮዳሄ ፋንታ ካህን አድርጎሃል።
የበቀል ወራት መጥቷል፥ የፍዳም ወራት ደርሶአል፥ እስራኤልም ይወቀው፤ ከበደልህና ከጥላቻህ ብዛት የተነሣ ነቢዩ ሞኝ ሆኗል፥ መንፈስም ያለበት ሰው አብዶአል።
ደቀመዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባርያም እንደ ጌታው ከሆነ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔልዜቡል ካሉት፥ ቤተሰቦቹንማ እንዴት ከዚህ የበለጠ አይሉአቸው?
አይሁድ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን አወቅን። አብርሃም እንኳን ሞተ፤ ነቢያትም እንዲሁ፤ አንተ ግን ‘ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘለዓለም ሞትን አይቀምስም፤’ ትላለህ።