Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 15:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በዋዘኞች ጉባኤ አልተቀመጥኩም አልተደሰትኩምም፤ ቁጣን ሞልተህብኛልና እጅህ በእኔ ላይ ስለ ሆነ ለብቻዬ ተቀመጥሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ፈንጠዝያ ከሚያደርጉት ጋራ አልተቀመጥሁም፤ ከእነርሱም ጋራ አልፈነጨሁም፤ እጅህ በላዬ ስለ ነበር፣ በቍጣህ ስለ ሞላኸኝ፣ ለብቻዬ ተቀመጥሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ከሚፈነጥዙ ሰዎች ጋር አልተወዳጀሁም፤ ከእነርሱም ጋር አልተደሰትኩም፤ ቊጣህ በእኔ ላይ ስለ ሆነ ብቻዬን ተቀመጥኩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በዋ​ዘ​ኞች ጉባኤ አል​ተ​ቀ​መ​ጥ​ሁም፤ ነገር ግን በእ​ጅህ ፊት ፈር​ቻ​ለሁ፤ ምሬ​ትን ሞል​ተ​ህ​ብ​ኛ​ልና ለብ​ቻዬ ተቀ​መ​ጥሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በዋዘኞችና በደስተኞች ጉባኤ አልተቀመጥሁም፥ ቍጣን ሞልተህብኛልና በእጅህ ፊት ለብቻዬ ተቀመጥሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 15:17
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮድ። እርሱ አሸክሞታልና ዝም ብሎ ለብቻው ይቀመጥ።


ብፁዕ ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በፌዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ።


ስለዚህም ጌታ ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ፤ ርኩስንም አትንኩ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፥


ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፤ የጌታም መንጋ ተማርኮአልና ዓይኔ እጅግ ታነባለች፥ እንባንም ታፈስሳለች።


ስለዚህ በጌታ ቁጣ ተሞልቻለሁ፤ ከመታገሥ ደክሜአለሁ፤ “በጎዳና ባሉ ሕፃናት ላይ በጉልማሶችም ጉባዔ ላይ በአንድነት አፍስሰው፤ ደግሞም ባል ከሚስቱ ጋር ሽማግሌውም በእድሜአቸው ከገፉት ጋር ይያዛሉና።


እንደ ምድረ በዳ እርኩም መሰልሁ፥ በፈረሰ ቤት እንዳለ እንደ ጉጉት ሆንሁ።


ለመብላትና ለመጠጣት፥ ከእነርሱም ጋር ለመቀመጥ ወደ ግብዣ ቤት አትግባ።


እነሆ፥ ዛሬ በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ እንድትነቅልና እንድታፈርስ፥ እንድታጠፋና እንድትገለባብጥ፥ እንድታንጽና እንድትተክል ሾሜሃለሁ።”


የጌታም መልአክ መልሶ፦ “አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ፥ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን የኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው?” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች