Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 11:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤ እነርሱም ‘እነሆ በላተኛና ጠጪ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ’ አሉት። ጥበብ በሥራዋ ጸደቀች።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤ እነርሱም፣ ‘በልቶ የማይጠግብ፣ ጠጪ እንዲሁም የቀረጥ ሰብሳቢዎችና የኀጢአተኞች ወዳጅ’ አሉት። ጥበብ ትክክለኛ መሆኗ ግን በሥራዋ ተረጋገጠ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 የሰው ልጅ ደግሞ እየበላና እየጠጣ ቢመጣ፥ ‘እነሆ! ይህ መብልና መጠጥ የሚወድ ነው! የቀራጮችና የኃጢአተኞችም ወዳጅ ነው!’ አሉት። ሆኖም የጥበብ ትክክለኛነት ግን በሥራዋ ይረጋገጣል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤ እነርሱም ‘እነሆ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኀጢአተኞች ወዳጅ’ ይሉታል። ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፥ እነርሱም፦ እነሆ፥ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ ይሉታል። ጥበብም በልጆችዋ ጸደቀች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 11:19
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁሉም አይተው “ከኀጢአተኛ ሰው ጋር ሊውል ገባ፤” ብለው አንጐራጐሩ።


በሰንበትም ቀን ከፈሪሳውያን አለቆች ወደ አንዱ ቤት ምግብ ሊበላ በገባ ጊዜ እነርሱ ይጠባበቁት ነበር።


የሰማውም ሕዝብ ሁሉ፥ ቀራጮች እንኳ ሳይቀሩ፥ በዮሐንስ ጥምቀት በመጠመቃቸው የእግዚአብሔርን ጻዲቅነት ተቀበሉ፤


በአስተዋይ ፊት ጥበብ ትኖራለች፥ የሰነፍ ዐይን ግን በምድር ዳርቻ ነው።


እያንዳንዳችን እንድናንጸው እርሱን ለመጥቀም ባልንጀራችንን ደስ እናሰኝ።


ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።


“አሜን ውዳሴ፥ ክብር፥ ጥበብ፥ ምስጋና ገናናነት፥ ክብር ኃይልና ብርታት ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ለአምላካችን ይሁን! አሜን።” አሉ።


ሰካራሞችና ሆዳሞች ይደኸያሉና፥ የእንቅልፍም ብዛት የተቦጫጨቀ ጨርቅ ያስለብሳልና።


የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ሽልማት ታገኛላችሁ? ቀራጮች እንኳ ይህንኑ ያደርጉ የለምን?


ይህ ቅጣት በሚከሱኝና በነፍሴም ላይ ክፉን በሚናገሩ ላይ ከጌታ ዘንድ ይሁን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች