ሉቃስ 23:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ ስለ አደረግነው የሚገባንን እየተቀበልን ነው፤ በእኛ ላይ የተወሰነው ትክክለኛ ፍርድ ነው፤ ይህ ሰው ግን ምንም ክፋት አልሠራም፤” ብሎ ገሠጸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ ላደረግነው ነገር ቅጣት እየተቀበልን ስለ ሆነ፣ ተገቢ ፍርድ ላይ ነን፤ ይህ ሰው ግን አንዳች ክፉ ነገር አላደረገም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ ባደረግነው በደል ምክንያት የሚገባንን ቅጣት አግኝተናል፤ ይህ ሰው ግን ምንም ጥፋት አላደረገም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእኛስ በሚገባ ተፈርዶብናል፤ እንደ ሥራችንም ፍዳችንን ተቀበልን፤ ይህ ግን ምንም የሠራው ክፉ ሥራ የለም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ አደረግነውም የሚገባንን እንቀበላለንና በእኛስ እውነተኛ ፍርድ ነው፤ ይህ ግን ምንም ክፋት አላደረገም ብሎ ገሠጸው። |
በክፉ ሥራችንና በታላቁ በደላችን ከደረሰብን ነገር ሁሉ በኋላ፥ አንተ አምላካችን እንደ ኃጢአታችን ብዛት አልቀሠፍኸንም ነገር ግን ትሩፋንን ሰጠኸን።
በየስፍራቸውም ቆመው የጌታ አምላካቸውን የሕግ መጽሐፍ የቀኑ ሩብ ያህል አነበቡ፥ የቀኑ ሩብ ደግሞ እየተናዘዙና፥ ለጌታ አምላካቸው እየሰገዱ አሳለፉ።
እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ፥ ሚስቱ “በእርሱ ምክንያት ዛሬ በሕልም ብዙ ተሠቃይቻለሁና በዚያ ጻድቅ ላይ ምንም እንዳታደርግ” ስትል ላከችበት።
ጲላጦስም ይህ ነገር ሁከት ከማስነሳት በስተቀር ምንም እንደማይጠቅም ባየ ጊዜ፥ ውሃ ወስዶ “እኔ ከዚህ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ ጉዳዩ የእናንተ ነው፤” ብሎ በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ።
የመቶ አለቃውና ከእርሱም ጋር ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩት የምድርን መናወጥና የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተው “በእውነት ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነበር” አሉ።