Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 23:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 በእ​ኛስ በሚ​ገባ ተፈ​ር​ዶ​ብ​ናል፤ እንደ ሥራ​ች​ንም ፍዳ​ች​ንን ተቀ​በ​ልን፤ ይህ ግን ምንም የሠ​ራው ክፉ ሥራ የለም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 እኛ ላደረግነው ነገር ቅጣት እየተቀበልን ስለ ሆነ፣ ተገቢ ፍርድ ላይ ነን፤ ይህ ሰው ግን አንዳች ክፉ ነገር አላደረገም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 እኛ ስለ አደረግነው የሚገባንን እየተቀበልን ነው፤ በእኛ ላይ የተወሰነው ትክክለኛ ፍርድ ነው፤ ይህ ሰው ግን ምንም ክፋት አልሠራም፤” ብሎ ገሠጸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 እኛ ባደረግነው በደል ምክንያት የሚገባንን ቅጣት አግኝተናል፤ ይህ ሰው ግን ምንም ጥፋት አላደረገም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 ስለ አደረግነውም የሚገባንን እንቀበላለንና በእኛስ እውነተኛ ፍርድ ነው፤ ይህ ግን ምንም ክፋት አላደረገም ብሎ ገሠጸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 23:41
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ ክፉ ሥራ​ች​ንና ስለ ታላቁ በደ​ላ​ችን ካገ​ኘን ነገር ሁሉ በኋላ፥ አንተ አም​ላ​ካ​ችን እንደ ኀጢ​አ​ታ​ችን ብዛት አል​ቀ​ሠ​ፍ​ኸ​ንም፤ ነገር ግን ድኅ​ነ​ትን ሰጠ​ኸን።


ጲላጦስም ሁከት እንዲጀመር እንጂ አንዳች እንዳይረባ ባየ ጊዜ፥ ውሃ አንሥቶ “እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ እናንተ ተጠንቀቁ፤” ሲል በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ።


“ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ፤” አለ። እነርሱ ግን “እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ፤” አሉ።


እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤


የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው “ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ፤” ብለው እጅግ ፈሩ።


እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ “ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ፤” ብላ ላከችበት።


በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸ​ውም ቆመው የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሕግ መጽ​ሐፍ አነ​በቡ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተና​ዘዙ፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገዱ።


በተ​ጨ​ነ​ቀም ጊዜ አም​ላ​ኩን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈለገ፤ በአ​ባ​ቶ​ቹም አም​ላክ ፊት ሰው​ነ​ቱን እጅግ አዋ​ረደ።


ጓደ​ኛ​ውም መልሶ ገሠ​ጸው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አንተ በዚህ ፍርድ ውስጥ ሳለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክ​ህን አት​ፈ​ራ​ው​ምን?


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም፥ “አቤቱ፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ትህ በመ​ጣህ ጊዜ ዐስ​በኝ” አለው።


በእናንተ በምታምኑ ዘንድ እንዴት ባለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ኑሮ እንደ ሄድን፥ እናንተና እግዚአብሔር ምስክሮች ናችሁ፤


ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች