Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ተሰሎንቄ 2:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በእናንተ በአማኞች መካከል እንዴት ባለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ኑሮ እንደ ነበርን እናንተና እግዚአብሔር ምስክሮች ናችሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በእናንተ በምታምኑት መካከል ሳለን እንዴት በቅድስና፣ በጽድቅ እንዲሁም ያለ ነቀፋ ሆነን እንደ ኖርን እናንተም እግዚአብሔርም ምስክሮች ናችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በእናንተ በአማኞች መካከል በነበርንበት ጊዜ እንዴት ባለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ሕይወት እንደ ኖርን እናንተ ምስክሮች ናችሁ፤ እግዚአብሔርም ምስክር ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በእናንተ በምታምኑ ዘንድ እንዴት ባለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ኑሮ እንደ ሄድን፥ እናንተና እግዚአብሔር ምስክሮች ናችሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በእናንተ በምታምኑ ዘንድ በእንዴት ያለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ኑሮ እንደ ሄድን፥ እናንተና እግዚአብሔር ምስክሮች ናችሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ተሰሎንቄ 2:10
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በእናንተ ኀላፊነት ሥር ላለው ለመንጋው መልካም ምሳሌ በመሆን እንጂ በኃይል በመግዛት አይሁን።


ወንጌላችን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ፥ በብዙም መረዳት እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ ስለ እናንተ ስንል በእናንተ መካከል ምን ዓይነት ሰዎች እንደ ነበርን እናንተው ታውቃላችሁ።


ትምክህታችን ይህ ነው፦ በዚህ ዓለም ይልቁንም በእናንተ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሥጋዊ ጥበብ ባልሆነ፥ በእግዚአብሔር ቅድስናና ቅንነት እንደኖርን፥ የሕሊናችን ምስክርነት ነው።


አንተ ግን ትምህርቴንና አካሄዴን ዓላማዬንም፥ እምነቴንም፥ ትዕግሥቴንም፥ ፍቅሬንም፥ መጽናቴንም፥


ወደ እርሱም በመጡ ጊዜ እንዲህ አላቸው “ወደ እስያ ከገባሁበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ፥ በትሕትና ሁሉና በእንባ ከአይሁድም ሤራ በደረሰብኝ ፈተና ለጌታ እየተገዛሁ ዘመኑን ሁሉ ከእናንተ ጋር እንዴት እንደኖርሁ እናንተው ታውቃላችሁ፤


ማንም ወጣትነትህን አይናቀው፤ ይልቅስ በንግግር፥ በኑሮ፥ በፍቅር፥ በእምነት፥ በንጽሕና፥ ለሚያምኑት ምሳሌ ሁን።


ስለዚህም እኛን ልትመስሉ እንዴት እንደሚገባችሁ እናንተው ራሳችሁ ታውቃላችሁ፤ በእናንተ ዘንድ በነበርንበት ጊዜ ሥራ ፈቶች አልነበርንም፤


እንደምታውቁት፥ የቁልምጫን ቃል ለስግብግብነትም ማመካኛ የሚሆን ነገር ከቶ አልተገኘብንም፥ እግዚአብሔርም ምስክር ነው።


ስለምን? ስለማልወዳችሁ ይመስላችኋል? እንደምወዳችሁ እግዚአብሔር ያውቃል።


በልባችሁ ስፍራ አኑሩን፤ ማንንም አልበደልንም፤ ማንንም አላጭበረበርንም፤ ማንንም መጠቀሚያ አላደረግንም።


ስለዚህ እኔ ደግሞ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ ነውር የሌለባት ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እተጋለሁ።


ስለዚህ እኔ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ እንደሆንሁ ዛሬ በዚች ቀን እመሰክርላችኋለሁ።


ለነፍሴ ጉድጓድ ቈፍረዋልና በውኑ በመልካም ፋንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም ለመናገር ቁጣህንም ከእነርሱ ለመመለስ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስታውስ።


ሙሴም እጅግ ተቈጣ፥ ጌታንም እንዲህ አለው፦ “ወደ ቁርባናቸው አትመልከት፤ እኔ ከእነርሱ አንድ አህያ እንኳ አልወሰድሁም፥ ከእነርሱም አንድ ሰው አልበደልሁም።”


ለዘለዓለም የተባረከ አምላክ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እንዳልዋሸሁ ያውቃል።


እንግዲህ የጌታን ፍርሃት አውቀን፥ ሰዎችን ለማስረዳት እንጥራለን፤ ስለ ራሳችን ከሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ የተገለጥን ነን፤ ለእናንተም ሕሊና የተገለጥን እንደ ሆንን ተስፋ አደርጋለሁ።


የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናል፤ በተንኮል አንመላለስም ወይም የእግዚአብሔርን ቃል በውሸት አንቀላቅልም፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን እናቀርባለን።


እኛ ስለ አደረግነው የሚገባንን እየተቀበልን ነው፤ በእኛ ላይ የተወሰነው ትክክለኛ ፍርድ ነው፤ ይህ ሰው ግን ምንም ክፋት አልሠራም፤” ብሎ ገሠጸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች