የሰሙትም ሁሉ እረኞቹ በነገሩአቸው ነገር ተደነቁ፤
ይህንም የሰሙ ሁሉ እረኞቹ በነገሯቸው ነገር ተደነቁ፤
ይህንንም የሰሙ ሁሉ እረኞቹ ባወሩላቸው ነገር ተደነቁ።
የሰሙትም ሁሉ እረኞቹ የነገሩአቸውን አደነቁ።
የሰሙትን ሁሉ እረኞቹ በነገሩአቸው ነገር አደነቁ፤
እነሆ፤ እኔና ጌታ የሰጠኝ ልጆች በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ለእስራኤል ምልክትና ድንቅ ነን።
አይተውም ስለዚህ ሕፃን የተነገራቸውን ቃል ገለጡ።
ማርያም ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰላሰለች ትጠብቀው ነበር።
ዮሴፍና እናቱም ስለ እርሱ በተባሉት ነገሮች ይደነቁ ነበር።
የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሶቹ ተገረሙ።
ሁሉም ተደነቁ፤ እርስ በርሳቸውም፦ “ይህ ቃል ምንድነው? በሥልጣንና በኃይል ርኩሳን መናፍስትን ያዝዛል፥ እነርሱም ይወጣሉ፤” እያሉ ይነጋገረሩ ነበር።