ሉቃስ 18:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜም አየ፤ እግዚአብሔርንም እያወደሰ ተከተለው። ሕዝቡም ሁሉ ይህን አይተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየውም ወዲያውኑ ማየት ቻለ፤ እግዚአብሔርንም እያከበረ ኢየሱስን ተከተለው። ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲያዩ እግዚአብሔርን አመሰገኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐይነ ስውሩም ወዲያውኑ ማየት ቻለ፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ኢየሱስን መከተል ጀመረ፤ ሕዝቡም ሁሉ ይህን ባዩ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜም አየ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነ፤ ተከተለውም፤ ሕዝቡም ሁሉ አይተው እግዚአብሔርን አመሰገኑት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም አየ፥ እግዚአብሔንም እያከበረ ተከተለው። ሕዝቡም ሁሉ አይተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ። |
ዕውሮችንም በማያውቁት መንገድ አመጣቸዋለሁ፤ በማያውቁትም ጎዳና እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፤ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፥ አልተዋቸውም።
ወደ ደብረዘይት ቁልቁለትም ወዲያው በቀረበ ጊዜ፥ ደቀመዛሙርቱ በሙሉ ስላዩአቸው ተአምራት ደስ እያላቸው በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን ማመስገን ጀመሩ፤
እነርሱም እንደምን እንደሚቀጡ ምክንያት ስላላገኙባቸው፥ እንደገና ዝተው ከሕዝቡ የተነሣ ፈቱአቸው፤ ሰዎች ሁሉ ስለ ሆነው ነገር እግዚአብሔርን ያከብሩ ነበርና።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችሁ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።