ሉቃስ 16:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጋቢውም በልቡ ‘ጌታዬ መጋቢነቱን ከእኔ ይወስዳልና ምን ላድርግ? ለመቈፈር ኃይል የለኝም፤ መለመንም አፍራለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “መጋቢውም በልቡ እንዲህ አለ፤ ‘ጌታዬ ከመጋቢነት ሊሽረኝ ነው፤ ለማረስ ጕልበት የለኝም፤ መለመን ደግሞ ዐፍራለሁ፤ ስለዚህ ምን ላድርግ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መጋቢውም በልቡ እንዲህ ሲል አሰበ፤ ‘አሁን እንግዲህ ጌታዬ ከመጋቢነት ሥራዬ ሊያሰናብተኝ ነው፤ ታዲያ ምን ባደርግ ይሻላል? ለመቈፈር ዐቅም የለኝም፤ አልችልም፤ መለመን ደግሞ ያሳፍረኛል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያም መጋቢ ዐስቦ እንዲህ አለ፦ ‘ምን ላድርግ? አሁን ጌታዬ ከመጋቢነቴ ይሽረኛል፤ ማረስ አልችልም፤ ለመለመንም አፍራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጋቢውም በልቡ፦ ጌታዬ መጋቢነቱን ከእኔ ይወስዳልና ምን ላድርግ? ለመቈፈር ኃይል የለኝም፥ መለመንም አፍራለሁ። |
በምትጎበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል? ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ? ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?
ከዚህ በኋላ ወደ ኢያሪኮ መጡ። ኢየሱስና ደቀመዛሙርቱ ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጡ ዐይነ ስውሩ የጤሜዎስ ልጅ በርጤሜዎስ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር።
ወደ መቅደስም ከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ፥ ሰዎች ተሸክመው መልካም በሚሉአት በመቅደስ ደጅ በየቀኑ ያስቀምጡት የነበሩ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ አንድ ሰው ነበረ።
እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ “ጌታ ሆይ! ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?” አለው። ጌታም “ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል፤” አለው።
ይህም የሆነው ሥራ ፈትተው ሥራን ከቶ የማይሰሩ ይልቁንም በሰው ነገር ጣልቃ የሚገቡ አንዳንዶች በእናንተ መካከል እንደሚኖሩ ስለ ሰማን ነው።