Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 12:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እርሱም ‘ፍሬዬን የማከማችበት ስፍራ አጥቻለሁና ምን ላድርግ?’ ብሎ በልቡ አሰበ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ይህም ሰው፣ ‘ምርቴን የማከማችበት ስፍራ ስለሌለኝ ምን ላድርግ?’ ብሎ በልቡ ዐሰበ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እርሱም በሐሳቡ፥ ‘ይህን ሁሉ እህል የማከማችበት ስፍራ ስለሌለኝ ምን ላድርግ?’ እያለ ያሰላስል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እህ​ሌን የማ​ኖ​ር​በት የለ​ኝ​ምና ምን ላድ​ርግ ብሎ በልቡ ዐሰበ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እርሱም፦ ፍሬዬን የማከማችበት ስፍራ አጥቻለሁና ምን ላድርግ? ብሎ በልቡ አሰበ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 12:17
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለሚጠይቅህ ስጥ፤ ከአንተ ሊበደር ከሚፈልገው ፊትህን አታዙር።


እንጀራህንስ ለተራበ እንድትቈርስ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ እንድታስገባ፥ የተራቈተውን ብታይ እንድታለብሰው፥ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?


እርሱ ስለ እኛ ሕይወቱን አሳልፎ ስለ ሰጠን በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ሕይወታችንን አሳልፈን ልንሰጥ ይገባናል።


ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ተቀበሉ።


ወደ ውጭም አውጥቶ “ጌቶች ሆይ! እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል?” ኣላቸው።


እርሱም ‘መልካም፥ አንተ በጎ አገልጋይ፥ በጥቂት ነገር የታመንህ ስለ ሆንክ በዐሥር ከተማዎች ላይ ሥልጣን ሰጥቼሃለሁ፤’ አለው።


ኢየሱስም ይህን ሰምቶ “አንዲት ነገር ገና ቀርታሃለች፤ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድኾች ስጥ፤ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፤ መጥተህም ተከተለኝ፤” አለው።


እኔም እላችኋለሁ፤ የዐመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘለዓለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ አማካኝነት ወዳጆችን ለራሳችሁ አብጁ።


በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑትን ሰዎች እንዳይታበዩ በሚያልፍም ባለጠግነት ላይ ሳይሆን እንድንደሰትበት ሁሉን አትረፍርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር ላይ ተስፋ እንዲያደርጉ እዘዛቸው።


ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተሰበረ፤ ጴጥሮስንና ሌሎችንም ሐዋርያት “ወንድሞች ሆይ! ምን እናድርግ?” አሉአቸው።


መጋቢውም በልቡ ‘ጌታዬ መጋቢነቱን ከእኔ ይወስዳልና ምን ላድርግ? ለመቈፈር ኃይል የለኝም፤ መለመንም አፍራለሁ።


ያላችሁን ሽጡ፤ ምጽዋትም ስጡ፤ ሌባ በማይቀርብበት ብልም በማያጠፋበት በሰማያት የማያልቅ መዝገብ የሚሆኑትን የማያረጁትንም ኮረጆዎች ለራሳችሁ አድርጉ፤


እናንተም የምትበሉትን የምትጠጡትንም አትፈልጉ፤ አታወላውሉም፤


ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ “ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ለነፍሳችሁ በምትበሉት ወይም ለሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ።


ነገር ግን በውስጥ ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ፤ እነሆም፥ ሁሉ ንጹሕ ይሆንላችኋል።


እነሆም፥ አንድ ሕግ አዋቂ ተነሥቶ ሊፈትነው እንዲህ አለ፦ “መምህር ሆይ! የዘለዓለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ?”


እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ሁለት ልብስ ያለው ምንም ለሌለው ያካፍል፤ ምግብም ያለው እንዲሁ ያድርግ።”


ለሰባት ደግሞም ለስምንት እድል ፈንታን ክፈል፥ በምድር ላይ የሚሆነውን ክፉ ነገር ምን እንደሆነ አታውቅምና።


እነርሱም እርስ በርሳቸው “እንጀራ ስላልያዝን ነው” ብለው አሰቡ።


ምሳሌም ነገራቸው እንዲህ ሲል “አንድ ባለ ጠጋ ሰው እርሻ እጅግ ፍሬያማ ሆነችለት።


‘እንዲህ አደርጋለሁ፤ ጎተራዬን አፍርሼ ሌላ የሚበልጥ እሠራለሁ፤ በዚያም ፍሬዬንና በረከቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች