Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 20:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ጌታ ሹሙን ‘ሠራተኞቹን ጥራና ኋላ ከመጡት ጀምረህ መጀመሪያ እስከመጡት ድረስ ደመወዝ ስጣቸው፤’ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ባለቤት የሠራተኞቹን ተቈጣጣሪ፣ ‘ኋላ ከመጡት ጀምረህ መጀመሪያ እስከመጡት ድረስ ያሉትን ሠራተኞች በሙሉ ጥራና ደመወዛቸውን ክፈላቸው’ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ባለቤት የሥራ ኀላፊውን ‘ሠራተኞቹን ጥራና በመጨረሻ ከተቀጠሩት ጀምረህ በፊት እስከ ተቀጠሩት ድረስ የሥራ ዋጋቸውን ክፈላቸው’ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ጌታ አዛዡን ‘ሠራተኞችን ጥራና ከኋለኞች ጀምረህ እስከ ፊተኞች ድረስ ደመወዝ ስጣቸው፤’ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ጌታ አዛዡን፦ ሠራተኞችን ጥራና ከኋለኞች ጀምረህ እስከ ፊተኞች ድረስ ደመወዝ ስጣቸው አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 20:8
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብራምም፦ አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ ምንን ትሰጠኛለህ? እኔም ያለ ልጅ እሄዳለሁ፥ የቤቴም መጋቢ የደማስቆ ሰው ይህ ኤልዔዘር ነው አለ።


ወደ ዮሴፍ ቤት አዛዥ ቀርበው፥ በቤቱ መግቢያ ላይ አነጋገሩት፤


“በባልንጀራህ ግፍ አታድርግ፥ አትቀማውም። ተቀጥሮ የሚያገለግለውን ሰው ደመወዙን እስከ ነገ ድረስ በአንተ ዘንድ አታቆይበት።


እነርሱም ‘የሚቀጥረን ስለ አጣን ነው፤’ አሉት። እርሱም ‘እናንተም ወደ ወይኔ አትክልት ቦታ ሂዱ፤’ አላቸው።


ዐሥራ አንድ ሰዓት ላይ የገቡት መጥተው እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ።


ከብዙ ጊዜ በኋላ የእነዚያ ባርያዎች ጌታ መጥቶ ከእነርሱ ጋር መተሳሰብ ጀመረ።


“የሰው ልጅ ከመላእክቱ ሁሉ ጋር በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ፥ ያንጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤


ለሠራተኛ ደሞዙ ይገባዋልና እነርሱ የሚሰጡአችሁን እየበላችሁና እየጠጣችሁ በዚያው ቤት ተቀመጡ። ከቤት ወደ ቤት አትዘዋወሩ።


ጌታም አለ “እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎቹ ላይ የሚሾመው ታማኝና ልባም መጋቢ ማን ነው?


የሄሮድስ መጋቢ የኩዛ ሚስት ዮሐና፥ ሶስናና ብዙዎች ሌሎችም ሆነው ከንብረታቸው በመጠቀም ያገለግሉአቸው ነበር።


መልካም ሆነ ወይም ክፉ፥ በሥጋችን እንደ ሠራነው ዋጋችንን ለመቀበል፥ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት እንቆማለን።


የሠራበትን ሒሣብ በዕለቱ፥ ፀሓይ ሳትጠልቅ ክፈለው፤ ድኻ በመሆኑ በጉጉት ይጠባበቀዋል። ያለበለዚያ ወደ ጌታ ይጮኽና ኃጢአት ይሆንብሃል።


ኤጲስ ቆጶስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ ነቀፋ የሌለበት ሊሆን ይገባዋል፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ ጠበኛ ያልሆነ፥ ለገንዘብ የማይስገበገብ፥


እንዲሁም ክርስቶስ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ተሰውቷል። ለሁለተኛ ጊዜ ሲታይ ሊያድናቸው ለሚጠባበቁት ኃጢአትን ለመሸከም ሳይሆን መዳንን ለማምጣት ነው።


የእግዚአብሔርን ልዩ ልዩ ጸጋ መልካም መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዱ ሰው በተቀበለው የጸጋ ስጦታ ሌላውን ያገልግል።


የአጫጆቹም አዛዥ፦ “ይህችማ ከሞዓብ ምድር ከናዖሚን ጋር የመጣች ሞዓባዊቱ ብላቴና ናት፥” ብሎ መለሰ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች