እሱም፦ “አንተን በእኛ ላይ አለቃና ዳኛ አድርጎ የሾመህ ማን ነው? ግብፃዊውን እንደ ገደልኸው ልትገድለኝ ትፈልጋለህን?” አለው። ሙሴም፦ “በእውነት ይህ ነገር ታውቆአል” ብሎ ፈራ።
ሉቃስ 12:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም “አንተ ሰው! ለዳኝነትና ለማከፋፈል ማን ነው በላያችሁ የሾመኝ?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም፣ “አንተ ሰው፤ በእናንተ ላይ ፈራጅ ወይም ዳኛ ያደረገኝ ማነው?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ግን፥ “አንተ ሰው፥ በእናንተ መካከል ፈራጅ እንድሆንና ርስት እንዳካፍል ማን ሾመኝ?” ሲል መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም፥ “አንተ ሰው፥ በእናንተ ላይ አካፋይና ዳኛ አድርጎ ማን ሾመኝ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ አንተ ሰው፥ ፈራጅና አካፋይ በላያችሁ አንድሆን ማን ሾመኝ? አለው። |
እሱም፦ “አንተን በእኛ ላይ አለቃና ዳኛ አድርጎ የሾመህ ማን ነው? ግብፃዊውን እንደ ገደልኸው ልትገድለኝ ትፈልጋለህን?” አለው። ሙሴም፦ “በእውነት ይህ ነገር ታውቆአል” ብሎ ፈራ።
ሰው ሆይ፥ መልካም ምን እንደሆነ ለአንተ ነግሮሃል፤ ፍትሕን እንድታደርግ፥ ምሕረትን እንድትወድና ከአምላክህም ጋር በትሕትና እንድትሄድ ካልሆነ በቀር ጌታ ከአንተ የሚፈልገው ምንድነው?
ስለዚህ አንተ የምትፈርድ ሰው ሆይ! የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው ላይ በምትፈርድበት ነገር በራስህ ላይ ትፈርዳለህ፤ ፈራጅ የሆንከው አንተ ያንኑ ታደርጋለህና።
ነገር ግን፥ ሰው ሆይ! ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥ አንተ ማን ነህ? የተሠራ ነገር የሠራውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ይለዋልን?