Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሮሜ 9:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ነገር ግን፥ ሰው ሆይ! ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥ አንተ ማን ነህ? የተሠራ ነገር የሠራውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ይለዋልን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ነገር ግን ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥ አንተ ማን ነህ? “ሥራ ሠሪውን፣ ‘ለምን እንዲህ ሠራኸኝ?’ ይለዋልን?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 አንተ ሰው! ከእግዚአብሔር ጋር ለመከራከር ምን መብት አለህ? የሸክላ ዕቃ ሠሪውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ሊለው ይችላልን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሰው ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ከ​ራ​ከ​ረው አንተ ምን​ድን ነህ? ሥራ ሠሪ​ውን እን​ዲህ አታ​ድ​ር​ገኝ ሊለው ይች​ላ​ልን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ነገር ግን፥ አንተ ሰው ሆይ፥ ለእግዚአብሔር የምትመልስ ማን ነህ? ሥራ ሠሪውን፦ ስለ ምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ ይለዋልን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሮሜ 9:20
30 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህ የእናንተ ጠማምነት ነው፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃ የምትቈጠሩ አይደላችሁምን? በውኑ ሥራ ሠሪውን፦ “አልሠራኸኝም” ይለዋልን? ወይስ የተደረገው አድራጊውን፦ “አታስተውልም” ይለዋልን?


አሁን ግን፥ አቤቱ ጌታ፥ አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን፤ አንተም ሠሪያችን ነህ፥ እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን።


አንተ፦ ‘በፍጹም ለቃሌ መልስ አይሰጥም’ ብለህ፥ ስለምን ከእርሱ ጋር ትከራከራለህ?


“በውኑ የሚከራከር ሰው ሁሉን የሚችል አምላክን መተቸት ይችላልን? ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋቀስ እርሱ ይመልስለት።”


የራሴ በሆነ ነገር ላይ የወደድሁትን ማድረግ አልችልምን? ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንኩ ትመቀኛለህን?


በውኑ ከንቱ ቃል መጨረሻ የለውምን? ወይስ ትመልስ ዘንድ ያነሣሣህ ምንድነው?


አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ ሰዎች መካከል የማያቋርጥ ጭቅጭቅን ነው፤ እንደነዚህ ያሉት ሰዎች እግዚአብሔርን መምሰል ሀብት ማግኛ ዘዴ መስሎ ይታያቸዋል።


ጥበበኛ የት አለ? ጻፊስ የት አለ? የዚህ ዘመን ተከራካሪስ የት አለ? እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን አላደረገምን?


በውኑ ፍርዴን ታፈርሳለህን? አንተስ ጻድቅ ትሆን ዘንድ በእኔ ላይ ትፈርዳለህን?


ማነው መንገዱን የሚያሳየው? ወይስ፦ ‘ተሳስተሃል’ የሚለው ማን ነው?


አንተ ከንቱ ሰው! እምነት ያለ ሥራ ዋጋ የሌለው መሆኑን ለማወቅ ማስረጃ ትፈልጋለህን?


ባርያዎች ለገዛ ጌቶቻቸው እንዲገዙና በነገር ሁሉ ደስ እንዲያሰኙአቸው ንገራቸው፤ እንዲሁም ሳይቃወሙና


ስለዚህ አንተ የምትፈርድ ሰው ሆይ! የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው ላይ በምትፈርድበት ነገር በራስህ ላይ ትፈርዳለህ፤ ፈራጅ የሆንከው አንተ ያንኑ ታደርጋለህና።


ሰው ሆይ፥ መልካም ምን እንደሆነ ለአንተ ነግሮሃል፤ ፍትሕን እንድታደርግ፥ ምሕረትን እንድትወድና ከአምላክህም ጋር በትሕትና እንድትሄድ ካልሆነ በቀር ጌታ ከአንተ የሚፈልገው ምንድነው?


አንድ ጊዜ ተናገርሁ፥ አልመልስምም፥ ሁለተኛ ጊዜም፥ ከእንግዲህ ወዲህ አልናገርም።”


ሚስት ሆይ! ባልሽን ታድኚ እንደሆን ምን ታውቂያለሽ? ወይስ ባል ሆይ! ሚስትህን ታድን እንደሆንህ ምን ታውቃለህ?


ንጉሡ ግን፥ “እናንት የጽሩያ ልጆች እኔ ከእናንተ ጋር ምን አለኝ? ጌታ፥ ‘ዳዊትን ርገመው’ ብሎት የሚረግመኝ ከሆነ፥ ‘ይህን ለምን አደረግህ’ ብሎ ማን ሊጠይቀው ይችላል?” አለው።


እንድመልስለት አብረን ወደ ፍርድ እንገባ ዘንድ፥ እርሱ እንደ እኔ ሰው አይደለም።


መጥረቢያ በሚቆርጥበት ሰው ላይ ይኩራራልን? መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን? በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፤ ዘንግም ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኩራራ ነው።


“የእስራኤል ቤት ሆይ! ይህ ሸክላ ሠሪ እንደሚሠራ በውኑ እኔ በእናንተ ላይ መሥራት አልችልምን? ይላል ጌታ፤ እነሆ፥ ጭቃው በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ፥ የእስራኤል ቤት ሆይ! እንዲሁ እናንተ በእኔ እጅ አላችሁ።


እርሱም “አንተ ሰው! ለዳኝነትና ለማከፋፈል ማን ነው በላያችሁ የሾመኝ?” አለው።


አንተም እንደዚህ በሚያደርጉ ላይ የምትፈርድ ያንንም የምታደርግ ሰው ሆይ! ከእግዚአብሔር ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃልን?


ወይም ሸክላ ሠሪ ከአንድ ዓይነት ጭቃ አንዱን ዕቃ ለክብር፥ አንዱን ደግሞ ለውርደት ሊሠራ በጭቃ ላይ መብት የለውምን?


ነገር ግን እግዚአብሔር ቁጣውን ለማሳየትና ኃይሉን ለማሳወቅ ፈልጎ፥ ለጥፋት የተዘጋጁትን የቁጣ ዕቃዎችን በብዙ ትዕግሥት ተቋቁሞ ቢሆንስ?


አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን ጌታ ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል።


በአንድ ትልቅ ቤት ውስጥ የወርቅና የብር ዕቃዎች ብቻ ሳይሆኑ የእንጨትና የሸክላ ዕቃዎችም ደግሞ ይኖራሉ፤ እኩሌቶቹም ለክብር፥ እኩሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች