Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 12:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ኢየሱስ ግን፥ “አንተ ሰው፥ በእናንተ መካከል ፈራጅ እንድሆንና ርስት እንዳካፍል ማን ሾመኝ?” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ኢየሱስም፣ “አንተ ሰው፤ በእናንተ ላይ ፈራጅ ወይም ዳኛ ያደረገኝ ማነው?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እርሱም “አንተ ሰው! ለዳኝነትና ለማከፋፈል ማን ነው በላያችሁ የሾመኝ?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አንተ ሰው፥ በእ​ና​ንተ ላይ አካ​ፋ​ይና ዳኛ አድ​ርጎ ማን ሾመኝ?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እርሱም፦ አንተ ሰው፥ ፈራጅና አካፋይ በላያችሁ አንድሆን ማን ሾመኝ? አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 12:14
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንተ ሰው! እንዲህ በሚያደርጉት ሰዎች ላይ እየፈረድክ፥ እነርሱ የሚያደርጉትን ስታደርግ ከእግዚአብሔር ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃልን?


አንተ ሰው! ከእግዚአብሔር ጋር ለመከራከር ምን መብት አለህ? የሸክላ ዕቃ ሠሪውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ሊለው ይችላልን?


በሌላው ሰው ላይ የምትፈርድ አንተ ለራስህ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው ሰው ላይ ስትፈርድ በራስህ ላይ ትፈርዳለህ፤ አንተ በሰው ላይ እየፈረድክ፥ ያ የፈረድክበት ሰው የሚያደርገውን ታደርጋለህ።


ሰውየውም “አንተን በእኛ ላይ ገዢና ዳኛ አድርጎ የሾመህ ማን ነው? ወይስ ያንን ግብጻዊ እንደ ገደልክ እኔንም መግደል ትፈልጋለህን?” አለው፤ ሙሴም እጅግ ፈርቶ “ያደረግኹት ነገር ታውቋል ማለት ነው” ብሎ አሰበ።


እርስዋም “ጌታ ሆይ! ማንም የለም” አለች። ኢየሱስም “እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ፤ ዳግመኛ ኃጢአት አትሥሪ” አላት።


ሰዎቹ ግን በግድ ወስደው ሊያነግሡት እንዳሰቡ ባወቀ ጊዜ ኢየሱስ ብቻውን እንደገና ራቅ ብሎ ወደ ኮረብታ ሄደ።


ኢየሱስ እምነታቸውን ባየ ጊዜ ሽባውን፥ “አንተ ሰው! ኃጢአትህ ተደምስሶልሃል፤” አለው።


እግዚአብሔር መልካም የሆነውንና ከአንተ የሚፈልገውን ነግሮሃል፤ ይኸውም ፍትሕን እንድትጠብቅ፥ ደግነትን እንድትወድ፥ ከአምላክህ ጋር በትሕትና እንድትመላለስ ነው።


ከጥቂት ጊዜ በኋላ አንድ ሌላ ሰው ጴጥሮስን አየውና “አንተም ከእነርሱ አንዱ ነህ!” አለው። ጴጥሮስ ግን “አንተ ሰው! አይደለሁም!” አለ።


ከሕዝቡም መካከል አንድ ሰው ኢየሱስን፦ “መምህር ሆይ፥ አባታችን ያወረሰንን ርስት እንዲያካፍለኝ እባክህ ለወንድሜ ንገረው” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች