ዳዊትም አንድ ሺህ ሠረገሎች፥ ሰባት ሺህ ፈረሰኞችና ሃያ ሺህ እግረኞች ማረከበት። ቁጥራቸው መቶ የሆነ የሠረገላ ፈረሶች ብቻ ሲቀሩ ሌሎቹን በሙሉ ቋንጃቸውን ቆረጠ።
ኢያሱ 11:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “ነገ በዚህ ጊዜ እኔ ሁሉንም እንደሞቱ አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና አትፍራቸው፤ የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ትቈርጣለህ፥ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ኢያሱን፣ “እነዚህን ሁሉ ነገ በዚች ሰዓት እንደ ሙት አድርጌ፣ በእስራኤል እጅ አሳልፌ ስለምሰጣቸው አትፍራቸው። የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሠረገሎቻቸውንም ታቃጥላለህ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ኢያሱን “እነርሱን አትፍራ፤ ስለ እስራኤል በመዋጋት ነገ ይህን ጊዜ ሁሉንም እንደ ሞቱ አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ አንተም የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሠረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “በእስራኤል ፊት ይሞቱ ዘንድ ነገ በዚህ ጊዜ ሁሉን በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና አትፍራቸው፤ የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ኢያሱን፦ ነገ በዚህ ጊዜ ሁሉን እንደ ሞቱ አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና አትፍራቸው፥ የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ትቈርጣለህ፥ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ አለው። |
ዳዊትም አንድ ሺህ ሠረገሎች፥ ሰባት ሺህ ፈረሰኞችና ሃያ ሺህ እግረኞች ማረከበት። ቁጥራቸው መቶ የሆነ የሠረገላ ፈረሶች ብቻ ሲቀሩ ሌሎቹን በሙሉ ቋንጃቸውን ቆረጠ።
ነገር ግን፦ “በፈረስ ላይ ተቀምጠን እንሸሻለን እንጂ እንዲህ አይሆንም” አላችሁ፥ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ደግሞም፦ “በፈጣን ፈረስ ላይ እንቀመጣለን” አላችሁ፥ ስለዚህም የሚያሳድዷችሁ ፈጣኖች ይሆናሉ።
ስለ እርዳታ ወደ ግብጽ ለሚወርዱ በፈረሶችም ለሚደገፉ፥ ስለ ብዛታቸውም በሰረገሎች፥ እጅግ ብርቱዎችም ስለ ሆኑ በፈረሰኞች ለሚታመኑ፥ ወደ እስራኤልም ቅዱስ ለማይመለከቱ ጌታንም ለማይፈልጉ ወዮላቸው!
በእስራኤልም ከተሞች የሚኖሩ ወጥተው፥ የጦር መሣሪያዎችን፥ አላባሽ ጋሻንና ጋሻን፥ ቀስትና ፍላጻዎችን፥ የእጅ በትሮችንና ጦርንም በእሳት ያቃጥላሉ፤ ሰባት ዓመት በእሳት ያቃጥሉአቸዋል።
ከእናንተ ጋር ቃላትን ውሰዱ፥ ወደ ጌታም ተመለሱ፥ እንዲህም በሉት፦ “በደልን ሁሉ አስወግድ፥ በቸርነትም ተቀበለን፥ በእንቦሳም ፋንታ የከንፈራችንን ፍሬ እንሰጣለን።
ጌታ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ የሚጥላቸውን ሕዝቦች ሁሉ ታጠፋቸዋለህ፥ ዓይንህም አታዝንላቸውም፤ ወጥመድ ይሆንብሃልና አማልክቶቻቸውን አታምልካቸው።
የአሮን ልጅ፤ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስም በፊቱ ይቆም ነበር። እስራኤላውያንም፥ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን እንደገና ሄደን ጦርነት እንግጠማቸው ወይስ ይቅር?” ሲሉ ጠየቁ። ጌታም፥ “ሂዱ፤ በነገው ዕለት በእጃችሁ እሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው።
ከዚያ ለመጡትም መልእክተኞች፥ “ለያቢሽ ገለዓድ ሰዎች፥ ‘ነገ ፀሓይ ሞቅ በሚልበት ጊዜ ነጻ ትሆናላችሁ’ ብላችሁ ንገሯቸው” አሏቸው። መልእክተኞቹም ሄደው ለያቢሽ ሰዎች ይህንኑ በነገሯቸው ጊዜ እጅግ ተደሰቱ።