የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዮናስ 1:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጌታ ቃል ወደ አሚታይ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ፦

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእግዚአብሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ለአሚታይ ልጅ ለዮናስ የገለጠለት የትንቢት ቃል ይህ ነው፦

ምዕራፉን ተመልከት

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦

ምዕራፉን ተመልከት



ዮናስ 1:1
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቀድሞ የእስራኤል ይዞታ የነበረውን በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ ጀምሮ በስተ ደቡብ እስከ ሙት ባሕር የሚገኘውን ግዛት ሁሉ ድል ነሥቶ እንደገና አስመለሰ፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው በጋትሔፌር ተወላጅ አገልጋይ በሆነው በአሚታይ ልጅ በነቢዩ ዮናስ አማካይነት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ነው።


አንበሳው አገሣ፤ የማይፈራ ማን ነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፤ ትንቢት የማይናገር ማን ነው?”


የጌታም ቃል ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ዮናስ መጣ፥ እንዲህ አለው፦


ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፤ ነገር ግን ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።” ከዚህ በኋላ ትቶአቸው ሄደ።


የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ይነሳሉ፥ በእርሱም ላይ ይፈርዳሉ፤ በዮናስ ስብከት ንስሓ ገብተዋልና፤ እነሆም፥ ከዮናስ የሚበልጥ በዚህ አለ።