Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




አሞጽ 3:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አንበሳው አገሣ፤ የማይፈራ ማን ነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፤ ትንቢት የማይናገር ማን ነው?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 አንበሳ አገሣ፤ የማይፈራ ማን ነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፤ ትንቢት የማይናገር ማን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 አንበሳ ሲያገሣ ሰምቶ የማይፈራ ማን አለ? ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ሲገልጥለት ትንቢት የማይናገር ማን አለ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 አን​በ​ሳው አገሣ፤ የማ​ይ​ፈራ ማን ነው? ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገረ፤ ትን​ቢት የማ​ይ​ና​ገር ማን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አንበሳው አገሣ፥ የማይፈራ ማን ነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፥ ትንቢት የማይናገር ማን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




አሞጽ 3:8
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም፤” አሉአቸው።


ወይስ አንበሳ የሚነጥቀው ነገር ሳያገኝ በጫካ ውስጥ ያገሣልን? ወይስ የአንበሳ ደቦል አንዳች ነገር ሳይዝ በማደርያው ሆኖ ይጮኻልን?


እኔም፦ “የጌታን ስም አላነሣም፥ ከእንግዲህ ወዲህም በስሙ አልናገርም” ብል፥ በአጥንቶቼ ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፤ ደከምሁ፥ መሸከምም አልቻልሁም።


እንዲህም አለ፦ “ጌታ በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፥ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ድምፁን ያስተጋባል፤ የእረኞችም ማሰማርያዎች ይጠወልጋሉ፥ የቀርሜሎስም ራስ ይደርቃል።”


ከሽማግሌዎቹም አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፥ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል፤” አለኝ።


ወንጌልን ብሰብክ እንኳ ግዴታዬ ነውና የምመካበት የለኝም፤ ወንጌልን ባልሰብክ ወዮልኝ!


እናንተ ግን ናዝራውያኑን የወይን ጠጅ አጠጣችሁ፤ ነቢያቱንም፦ ትንቢትን አትናገሩ፥ ብላችሁ አዘዛችሁ።


ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ “ከሰው ሥልጣን ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።


“ሂዱና ቆማችሁ የዚህን ሕይወት ቃል ሁሉ ለሕዝብ በመቅደስ ንገሩ፤” አላቸው።


ጌታም እንዲህ ይለኛልና፦ አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ ሲያገሣ፥ ብዙ እረኞች ቢከማቹበት ከቃላቸው እንደማይፈራ ከድምፃቸውም እንደማይዋረድ፥ እንደዚሁም የሠራዊት ጌታ በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ለመዋጋት ይወርዳል።


በዚያ ቀን ለእስራኤል ቤት ቀንድን አበቅላለሁ፥ ለአንተ ደግሞ በመካከላቸው የተከፈተ አፍን እሰጥሃለሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


እናንተ በአውድማዬ ላይ የተወቃችሁ የአውድማዬ ልጆች ሆይ፥ ከእስራኤል አምላክ ከሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሰማሁትን ነገርኳችሁ።


ኤርምያስም ለአለቆችና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ “የሰማችሁትን ቃላት ሁሉ በዚህች ቤትና በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት እንድናገር ጌታ ልኮኛል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች