እነሆ፥ እኔ የሽብር ወሬ የሚያሰማ መንፈስ እልክበታለሁ፤ ስለዚህም ወደ አገሩ ተመልሶ እንዲሄድና እዚያም በገዛ ምድሩ በሰይፍ ተመትቶ እንዲሞት አደርጋለሁ።’”
ኤርምያስ 51:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በባቢሎን ላይና በሌብ-ቃምያ በሚኖሩት ላይ አጥፊውን ነፋስ አስነሣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ በባቢሎንና በምድሯ ላይ፣ የሚያጠፋ ነፋስ አስነሣለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ባቢሎንና ሕዝብዋን ጠራርጎ የሚያጠፋ ብርቱ ነፋስ አስነሣለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ በባቢሎን ላይና በከለዳውያን ምድር በሚኖሩት ላይ የሚያቃጥልና የሚያጠፋ ነፋስን አስነሣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በባቢሎን ላይና በከለዳውያን ምድር በሚኖሩት ላይ አጥፊውን ነፋስ አስነሣለሁ። |
እነሆ፥ እኔ የሽብር ወሬ የሚያሰማ መንፈስ እልክበታለሁ፤ ስለዚህም ወደ አገሩ ተመልሶ እንዲሄድና እዚያም በገዛ ምድሩ በሰይፍ ተመትቶ እንዲሞት አደርጋለሁ።’”
አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ በትቢያም ላይ ተቀመጪ፤ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ ከዚህ በኋላ ቅንጡና ቅምጥል አትባይምና ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ።
ከአራቱም ከሰማይ ማዕዘናት አራቱን ነፋሳት በኤላም ላይ አመጣለሁ፥ ወደ እነዚያም ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ፤ ከኤላም የተሰደዱ ሰዎች ተሰድደው ያልደረሱበት ሕዝብ አይገኝም።
ቀስትን የሚገትሩትን ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው፤ በዙሪያዋ ስፈሩባት አንድም ሰው አያምልጥ፤ በእስራኤል ቅዱስ በጌታ ላይ በኩራት አልታዘዝም ብላለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፥ እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት።
የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች በአንድነት ተጨቊነዋል፥ የማረኳቸውም ሁሉ በኃይል ይዘዋቸዋል፥ እነርሱንም ለመልቀቅ እንቢ ብለዋል።
እነሆ፥ ከሰሜን ምድር የታላላቅ አሕዛብን ጉባኤ አስነሣለሁ በባቢሎንም ላይ አመጣቸዋለሁ፤ በእርሷም ላይ ይሰለፋሉ፥ ከዚያም ትያዛለች፤ ፍላጾቻቸውም ተጨናግፎ ባዶውን እንደማይመለስ እንደ ብልህ ጀግና ፍላጻ ናቸው።
በወንድሞቹ መካከል ፍሬያማ ቢሆንም እንኳ የምሥራቅ ነፋስ ይመጣል፥ የጌታ ነፋስ ከምድረበዳ ይመጣል፤ ፈሳሹንም ይጠፋል፥ ምንጩንም ይደርቃል፥ የተከበሩ ዕቃዎች ሁሉ ያሉበትን መዝገብ ይበዘብዛል።