ኤርምያስ 23:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 እነሆ፥ የጌታ ዐውሎ ነፋስ! ቁጣው ወጥቶአል፥ ጥቅል ዐውሎ ነፍስ፤ እርሱም በክፉዎች ራስ ላይ ይወርዳል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 እነሆ፤ የእግዚአብሔር ዐውሎ ነፋስ፣ በቍጣ ይነሣል፤ ብርቱም ማዕበል፣ የክፉዎችን ራስ ይመታል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 የእግዚአብሔር ቊጣ በክፉዎች ራስ ላይ እንደሚተም ማዕበልና እንደ ብርቱ ዐውሎ ነፋስ ሲወርድ ተመልከት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 እነሆ ከእግዚአብሔር ዘንድ ንውጽውጽታ ይመጣል፤ ኃጥኣንን ያነዋውጣቸውና ይገለብጣቸው ዘንድ መቅሠፍት ይመጣባቸዋል፤ የዐመፀኞችን ራስ ይገለባብጣል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 እነሆ፥ የእግዚአብሔር ዐውሎ ነፋስ፥ እርሱም ቍጣው፥ የሚያገለባብጥ ዐውሎ ነፍስ ወጥቶአል፥ የዓመፀኞችን ራስ ይገለባብጣል። ምዕራፉን ተመልከት |