እነሆ፥ አሁን እንኳ በአንዱ ዋሻ ወይም በሌላ ቦታ ተደብቆ ይሆናል። ጥቂት ሰዎች በመጀመሪያ በሚጥልባቸው ጥቃት ቢሞቱ ይህን የሰማ ሁሉ፥ ‘አቤሴሎምን የተከተለው ሠራዊት ተፈጀ’ ብሎ ያወራል።
ኤርምያስ 41:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር የገደላቸውን የሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣለበት ጉድጓድ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ለመመከት የሠራው ምሽግ ነበረ፤ የናታንያም ልጅ እስማኤል የገደላቸውን ሞላበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስማኤል ከጎዶልያስ በተጨማሪ የገደላቸው ሰዎች ሁሉ ሬሳ የተጣለበት የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓድ፣ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ስለ ፈራ ለመከላከል ያሠራው ነበር፤ ይህን ጕድጓድ የናታንያ ልጅ እስማኤል በሬሳ ሞላው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚያን ሰዎች ገድሎ የጣለበትም ያ ጒድጓድ የእስራኤል ንጉሥ ባዕሻ አደጋ በጣለበት ጊዜ ንጉሥ አሳ ለመጠባበቂያ አስቈፍሮት የነበረ ትልቅ ጒድጓድ ነበር፤ እስማኤል ያን ጒድጓድ በሬሳ ሞላው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር የገደላቸውን ሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣለበት ጕድጓድ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ስለ ፈራ የሠራው ጕድጓድ ነበረ፤ የናታንያም ልጅ እስማኤል የገደላቸውን ሞላበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር የገደላቸውን የሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣለበት ጕድጓድ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ስለ ፈራ የሠራው ጕድጓድ ነበረ፥ የናታንያም ልጅ እስማኤል የገደላቸውን ሞላበት። |
እነሆ፥ አሁን እንኳ በአንዱ ዋሻ ወይም በሌላ ቦታ ተደብቆ ይሆናል። ጥቂት ሰዎች በመጀመሪያ በሚጥልባቸው ጥቃት ቢሞቱ ይህን የሰማ ሁሉ፥ ‘አቤሴሎምን የተከተለው ሠራዊት ተፈጀ’ ብሎ ያወራል።
አንተ ግን እንደ ተጠላ ቅርንጫፍ ከመቃብርህ ተጥለሃል፤ በሰይፍም የተወጉት፥ ተገድለውም ወደ ጉድጓዱ ድንጋዮች የወረዱ ከድነውሃል፤ እንደተረገጠም ሬሳ ሆነሃል።
እስራኤላውያን ያሉበት ሁኔታ እጅግ አስጊ መሆኑንና ሠራዊታቸውም በከባድ ጭንቀት ውስጥ መግባቱን ባዩ ጊዜ፥ በየዋሻውና በየቁጥቋጦው፥ በየዐለቱ መካከልና በየገደሉ እንዲሁም በየጉድጓዱ ሁሉ ተሸሸጉ።
በተራራማው የኤፍሬም አገር ተሸሽገው የነበሩት እስራኤላውያን ሁሉ ፍልስጥኤማውያኑ በሽሽት ላይ መሆናቸውን በሰሙ ጊዜ፥ እነርሱም አጥብቀው በመከታተል ሊወጉአቸው አሳደዷቸው።
ስለዚህ ሳኦል ከመላው እስራኤል የተመረጡ ሦስት ሺህ ሰዎችን ይዞ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመፈለግ “የሜዳ ፍየሎች ዓለት” ወደ ተባለው ቦታ አቅራቢያ ሄደ።