1 ሳሙኤል 24:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ስለዚህ ሳኦል ከመላው እስራኤል የተመረጡ ሦስት ሺህ ሰዎችን ይዞ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመፈለግ “የሜዳ ፍየሎች ዓለት” ወደ ተባለው ቦታ አቅራቢያ ሄደ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ሳኦልም በመንገድ ዳር ወዳለው ወደ አንድ የበጎች ማደሪያ በደረሰ ጊዜ፣ ዋሻ አግኝቶ ወገቡን ሊሞክር ወደዚያ ገባ። ዳዊትና ሰዎቹም ከዋሻው በውስጠኛው ቦታ ተቀምጠው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 በመንገድ ዳር ባሉት የበጎች ማደሪያዎች አቅራቢያ ወደሚገኘው ወደ አንድ ዋሻ ወገቡን ሊሞክር ወደ ውስጥ ገባ፤ በዚያም እርሱ ከተቀመጠበት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ዳዊትና ተከታዮቹ ተደብቀው የሚኖሩበት ክፍል ነበር፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ሳኦልም ከእስራኤል ሁሉ የተመረጡትን ሦስት ሺህ ሰዎች ወሰደ፤ ዳዊትንና ሰዎቹንም ለመፈለግ ዋሊያዎች ወደሚታደኑባቸው ዓለቶች ሄደ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 በመንገድም አጠገብ ወዳሉት የበጎች ማደሪያዎች መጣ፥ በዚያም ዋሻ ነበረ፥ ሳኦልም ወገቡን ይሞክር ዘንድ ከዚያ ገባ፥ ዳዊትና ሰዎቹም ከዋሻው በውስጠኛው ቦታ ተቀምጠው ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |