የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 34:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እናንተም ዛሬ ተመልሳችሁ፥ ሰው ሁሉ ባልንጀራውን አርነት ለማውጣት አዋጅ በመንገር ለዓይኔ ደስ የሚያሰኝን ነገር አድርጋችሁ ነበር፥ ስሜም በተጠራበት ቤት ውስጥ በፊቴ ቃል ኪዳን አድርጋችሁ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እናንተም አሁን ንስሓ በመግባት በፊቴ ትክክለኛ ነገር አደረጋችሁ፤ እያንዳንዳችሁም ለወገኖቻችሁ ነጻነት ዐወጃችሁ፤ ስሜ በሚጠራበት ቤትም በፊቴ ቃል ኪዳን ገባችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነሆ እናንተም ከጥቂት ቀኖች በፊት ተጸጸታችሁ እኔን ደስ የሚያሰኝ ነገር መሥራት ጀምራችሁ ነበር፤ ሁላችሁም ከእስራኤላውያን ወገን የሆኑ ባሪያዎቻችሁን ነጻ ለመልቀቅ ተስማማችሁ፤ እኔ በምመለክበትም ቤተ መቅደስ ተሰብስባችሁ በፊቴ ቃል ኪዳን ገባችሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እና​ን​ተም ዛሬ ተመ​ል​ሳ​ችሁ ሰው ሁሉ ባል​ን​ጀ​ራ​ውን አር​ነት ለማ​ው​ጣት ዓመተ ኅድ​ገ​ትን በማ​ድ​ረግ በዐ​ይኔ ፊት ቅን የሆ​ነ​ውን ነገር አድ​ር​ጋ​ችሁ ነበር፤ ስሜም በሚ​ጠ​ራ​በት ቤት ውስጥ በፊቴ ቃል ኪዳን አድ​ር​ጋ​ችሁ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እናንተም ዛሬ ተመልሳችሁ ሰው ሁሉ ባልንጀራውን አርነት ለማውጣት አዋጅ በመንገር ለዓይኔ ደስ የሚያሰኝን ነገር አድርጋችሁ ነበር፥ በስሜም በሚጠራበት ቤት ውስጥ በፊቴ ቃል ኪዳን አድርጋችሁ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 34:15
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ካህኑ ዮዳሄ ይመክረውና ያስተምረው ስለ ነበር፥ ኢዮአስ በዕድሜው ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ፤


አሜስያስ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠርቶአል፤ ይሁን እንጂ እንደ ቀድሞ አያቱ እንደ ንጉሥ ዳዊት አልነበረም፤ እንደ ዳዊት በመሆን ፈንታ የአባቱን የኢዮአስን ፈለግ ተከተለ።


ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ በሙሉ ልቡና ሐሳቡ እግዚአብሔርን ለመከተልና ትእዛዞቹን፥ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን ለመጠበቅ በእርሱ ፊት ቃል ኪዳኑን አደሰ፤ ስለዚህም በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አረጋገጠ፤ ሕዝቡም በቃል ኪዳኑ ተባበረ።


የቀሩት ሕዝብ፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ በር ጠባቂዎቹ፥ መዘምራን፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች፥ ከምድር ሕዝቦች ወደ እግዚአብሔር ሕግ ራሳቸውን የለዩ ሁሉ፥ ሚስቶቻቸው፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው፥ የሚያውቁትና የሚያስተውሉት ሁሉ፥


የጽድቅህን ፍርድ እጠብቅ ዘንድ ማልሁ፥ አጸናሁም።


የሰውም ቁጣ ሳይቀር ክብርህን ይገልጣል፥ ከዚህ የሚተርፈውንም ትታጠቀዋለህ።


ነገር ግን ዕለት ዕለት ይሹኛል፤ መንገዴንም ለማወቅ ይወድዳሉ፤ ጽድቅን እንዳደረጉ የአምላካቸውንም ፍርድ እንዳልተዉ ሕዝቦች እውነተኛውን ፍርድ ይለምኑኛል፤ ወደ እግዚአብሔርም ለመቅረብ ይወዳሉ።


ሊያረክሱትም ስሜ በተጠራበት ቤት ውስጥ ርኩሰታቸውን አኖሩ።


ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው። ይህም ቃል የመጣው ለባርያዎች ስለ አርነታቸው አዋጅ እንዲነገር ንጉሡ ሴዴቅያስ በኢየሩሳሌም ከነበሩ ሕዝብ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን ካደረገ በኋላ ነው፤


ኀምሳኛውንም ዓመት ትቀድሳላችሁ፥ በምድሪቱም ለሚኖሩባት ሁሉ ነጻነትን ታውጃላችሁ፤ እርሱ ለእንናተ ኢዮቤልዩ ይሆናል፤ ከእናንተም እያንዳንዱ ሰው ወደ ርስቱና ወደ ወገኑ ይመለሳል።


“ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ እጅግ የራቀ ነው፤