ኤርምያስ 2:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንስ የሺሖርን ውኃ ለመጠጣት ወደ ግብጽ በመሄድሽ የምታገኚው ምን ነገር አለ? የኤፍራጥስንም ውኃ ለመጠጣት ወደ አሦር በመሄድሽ የምታገኚው ምን ነገር አለ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሺሖር ወንዝ ውሃ ለመጠጣት፣ አሁንስ ለምን ወደ ግብጽ ወረድሽ? ከኤፍራጥስ ወንዝስ ውሃ ለመጠጣት፣ ወደ አሦር መውረድ ለምን አስፈለገሽ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ግብጽ ወርደሽ ከዓባይ ወንዝ ውሃ መጠጣት የፈለግሽው ምን ጥቅም ለማግኘት ነው? ወደ አሦርስ ወርደሽ ከኤፍራጥስ ወንዝ ውሃ መጠጣት የፈለግሽው ምን የምታተርፊ መስሎሽ ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንስ የግዮንን ውኃ ትጠጪ ዘንድ በግብፅ መንገድ ምን ጉዳይ አለሽ? የወንዞችንም ውኃ ትጠጪ ዘንድ በአሦር መንገድ ምን ጉዳይ አለሽ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንስ የሺሖርን ውኃ ትጠጪ ዘንድ በግብጽ መንገድ ምን ጉዳይ አለሽ? የኤፍራጥስንም ውኃ ትጠጪ ዘንድ በአሦር መንገድ ምን ጉዳይ አለሽ? |
ስለ እርዳታ ወደ ግብጽ ለሚወርዱ በፈረሶችም ለሚደገፉ፥ ስለ ብዛታቸውም በሰረገሎች፥ እጅግ ብርቱዎችም ስለ ሆኑ በፈረሰኞች ለሚታመኑ፥ ወደ እስራኤልም ቅዱስ ለማይመለከቱ ጌታንም ለማይፈልጉ ወዮላቸው!
ነገር ግን በእርሱ ላይ ዐመጸ፥ ፈረሶችንና ብዙ ሕዝብም እንዲሰጡት መልእክተኞቹን ወደ ግብጽ ላከ። ይሳካለታልን? እነዚህን ነገሮች ያደረገስ ያመልጣልን? ቃል ኪዳንን አፍርሶስ ያመልጣልን?
ኤፍሬምም ደዌውን፥ ይሁዳም ቁስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፥ ወደ ታላቁም ንጉሥ መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ሊፈውሳችሁ፥ ከቁስላችሁም ሊያድናችሁ አልቻለም።
በግብጽ ፊት ለፊት ካለው ከሺሖር ወንዝ ጀምሮ በሰሜን በኩል እስካለችው የከነዓናውያን ሆና እስከ ተቈጠረችው እስከ አቃሮን ዳርቻ ድረስ፥ የጋዛ፥ የአዛጦን፥ የአስቀሎና፥ የጌት፥ የአቃሮን፥ አምስቱ የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ናቸው፥ የኤዋውያን የሆኑትም እንዲሁ፥