Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 2:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 አሁ​ንስ የግ​ዮ​ንን ውኃ ትጠጪ ዘንድ በግ​ብፅ መን​ገድ ምን ጉዳይ አለሽ? የወ​ን​ዞ​ች​ንም ውኃ ትጠጪ ዘንድ በአ​ሦር መን​ገድ ምን ጉዳይ አለሽ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከሺሖር ወንዝ ውሃ ለመጠጣት፣ አሁንስ ለምን ወደ ግብጽ ወረድሽ? ከኤፍራጥስ ወንዝስ ውሃ ለመጠጣት፣ ወደ አሦር መውረድ ለምን አስፈለገሽ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 አሁንስ የሺሖርን ውኃ ለመጠጣት ወደ ግብጽ በመሄድሽ የምታገኚው ምን ነገር አለ? የኤፍራጥስንም ውኃ ለመጠጣት ወደ አሦር በመሄድሽ የምታገኚው ምን ነገር አለ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ወደ ግብጽ ወርደሽ ከዓባይ ወንዝ ውሃ መጠጣት የፈለግሽው ምን ጥቅም ለማግኘት ነው? ወደ አሦርስ ወርደሽ ከኤፍራጥስ ወንዝ ውሃ መጠጣት የፈለግሽው ምን የምታተርፊ መስሎሽ ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 አሁንስ የሺሖርን ውኃ ትጠጪ ዘንድ በግብጽ መንገድ ምን ጉዳይ አለሽ? የኤፍራጥስንም ውኃ ትጠጪ ዘንድ በአሦር መንገድ ምን ጉዳይ አለሽ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 2:18
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በግ​ብፅ ፊት ካለው ምድረ በዳ ጀምሮ ለአ​ም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ግዛ​ቶች ለጋዛ፥ ለአ​ዛ​ጦን፥ ለአ​ስ​ቀ​ሎና፥ ለጌት፥ ለአ​ቃ​ሮን፥ እን​ዲ​ሁም ለኤ​ዌ​ዎ​ና​ው​ያን በተ​ቈ​ጠ​ረ​ችው በከ​ነ​ዓን ግራ በኩል እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አቃ​ሮን ዳርቻ ድረስ ነው፤


ኤፍ​ሬ​ምም ልብ እን​ደ​ሌ​ላት እንደ ሰነፍ ርግብ ነው፤ ግብ​ፅን ጠሩ፤ ወደ አሦ​ርም ሄዱ።


መን​ገ​ድ​ሽን እጥፍ ታደ​ርጊ ዘንድ ለምን እጅግ ትሮ​ጫ​ለሽ? በአ​ሦር እን​ዳ​ፈ​ርሽ በግ​ብ​ፅም ታፍ​ሪ​ያ​ለሽ።


ርዳታ ለመ​ፈ​ለግ ወደ ግብፅ ለሚ​ወ​ርዱ፥ በፈ​ረ​ሶ​ችና በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ለሚ​ታ​መኑ ወዮ​ላ​ቸው! ፈረ​ሰ​ኞቹ ብዙ​ዎች ናቸ​ውና፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ አል​ታ​መ​ኑ​ምና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ለ​ጉ​ምና።


ኤፍ​ሬ​ምም ደዌ​ውን አያት፤ ይሁ​ዳም ሥቃ​ዩን አያት፤ ኤፍ​ሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ወደ ንጉ​ሡም ወደ ኢያ​ሪም መል​እ​ክ​ተ​ኛን ላከ፤ እርሱ ግን ፈጽሞ ይፈ​ው​ሳ​ችሁ ዘንድ አል​ቻ​ለም፤ ከእ​ና​ን​ተም ሕማም አል​ተ​ወ​ገ​ደም።


እርሱ ግን በእ​ርሱ ላይ ሸፈተ፤ ፈረ​ሶ​ች​ንና ብዙ​ንም ሕዝብ ይሰ​ጡት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ወደ ግብፅ ላከ። በውኑ ይከ​ና​ወ​ን​ለት ይሆን? ይህ​ንስ ያደ​ረገ ያመ​ል​ጣ​ልን? ቃል ኪዳ​ን​ንስ ያፈ​ረሰ ያመ​ል​ጣ​ልን?


ፌ። በማ​ያ​ድን ወገን እያ​መ​ንን ረዳ​ታ​ችን ከንቱ ስለ ሆነ፥ እኛ ገና በሕ​ይ​ወት ሳለን ዐይ​ኖ​ቻ​ችን ጠፉ።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከወ​ንዙ ማዶ ባመ​ጣው ታላቅ ምላጭ በአ​ሦር ንጉሥ የራ​ሱ​ንና የእ​ግ​ሩን ጠጕር ይላ​ጨ​ዋል፤ ምላ​ጩም ጢሙን ደግሞ ይላ​ጫል።


የገቡ ስደ​ተ​ኞች አሕ​ዛብ በመ​ከር ጊዜ እን​ደ​ሚ​ለ​ወጥ ዘር ናቸው።


ከአ​ሦ​ራ​ው​ያን ልጆች ጋር ፈጽ​መሽ አመ​ነ​ዘ​ርሽ፤ ከዚ​ህም ጋር ገና አል​ጠ​ገ​ብ​ሽም፤ ዝሙ​ት​ሽም አል​በ​ቃ​ሽም።


በዚ​ያም ጊዜ ንጉሡ አካዝ ርዳታ ፈልጎ ወደ አሦር ንጉሥ ላከ፤


አንቺ ከዳ​ተኛ ልጅ ሆይ! እስከ መቼ ትቅ​በ​ዘ​በ​ዣ​ለሽ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥ​ሮ​አ​ልና ሰው ወደ ድኅ​ነት ይመ​ጣል።”


ግብ​ፃ​ው​ያ​ንና አሦ​ራ​ው​ያን፥ እን​ጀ​ራን ያጠ​ግ​ቡን ዘንድ እጃ​ቸ​ውን ሰጡን።


ከአ​ሕ​ዝብ ጋር ስላ​መ​ነ​ዘ​ርሽ፤ በበ​ደ​ላ​ቸ​ውም ስለ ረከ​ስሽ ይህን ያደ​ር​ጉ​ብ​ሻል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች