ሆሴዕ 7:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ኤፍሬምም አእምሮ እንደሌለው እንደ ሞኝ ርግብ ነው፤ ግብጽን ጠሩ፥ ወደ አሦርም ሄዱ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 “ኤፍሬም በቀላሉ እንደምትታለል፣ አእምሮም እንደሌላት ርግብ ነው፤ አንድ ጊዜ ወደ ግብጽ ይጣራል፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ አሦር ይዞራል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 የእስራኤል ሕዝብ እንደ ርግብ የዋህና አእምሮ የጐደላቸው ሆነዋል፤ ስለዚህም ርዳታ ለማግኘት አንድ ጊዜ ወደ ግብጽ ይጣራሉ፤ አንድ ጊዜም ወደ አሦር ይበራሉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ኤፍሬምም ልብ እንደሌላት እንደ ሰነፍ ርግብ ነው፤ ግብፅን ጠሩ፤ ወደ አሦርም ሄዱ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ኤፍሬምም አእምሮ እንደሌላት እንደ ሰነፍ ርግብ ነው፥ ግብጽን ጠሩ፥ ወደ አሦርም ሄዱ። ምዕራፉን ተመልከት |