ዘፍጥረት 7:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍጥረት ሁሉ ወንድና ሴት ሆነው ወደ መርከቡ የገቡት እግዚአብሔር እንዳዘዘው ገቡ፤ ጌታም በስተ ኋላው ዘጋበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሕያዋንም ፍጥረታት ሁሉ እግዚአብሔር ኖኅን ባዘዘው መሠረት ተባዕትና እንስት እየሆኑ ገቡ፤ ከዚያም እግዚአብሔር ከውጭ ዘጋበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍጥረት ሁሉ ወንድና ሴት ሆነው ወደ መርከቡ የገቡት እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ነው፤ ከዚህ ቀጥሎ እግዚአብሔር ከኖኅ በስተኋላ የመርከቡን በር ዘጋ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥጋ ካለው ሁሉ የገቡትም ተባትና እንስት እግዚአብሔር ኖኅን እንዳዘዘው ገቡ፤ እግዚአብሔር አምላክም መርከብዋን በስተውጭ ዘጋት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥጋ ካለው ሁሉ የገቡትም ተባትና እንስት እግዚአብሔርም በስተ ኋላው ዘጋበት። |
ባለቤቱ ተነሥቶ በሩን ከቈለፈ በኋላ፥ እናንተ በውጭ ቆማችሁ ‘ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! ክፈትልን’ እያላችሁ በሩን ማንኳኳት ትጀምራላችሁ፤ እርሱም መልሶ ‘ከየት እንደ ሆናችሁ አላውቅም’ ይላችኋል።