Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 7:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ፍጥረት ሁሉ ወንድና ሴት ሆነው ወደ መርከቡ የገቡት እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ነው፤ ከዚህ ቀጥሎ እግዚአብሔር ከኖኅ በስተኋላ የመርከቡን በር ዘጋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከሕያዋንም ፍጥረታት ሁሉ እግዚአብሔር ኖኅን ባዘዘው መሠረት ተባዕትና እንስት እየሆኑ ገቡ፤ ከዚያም እግዚአብሔር ከውጭ ዘጋበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ፍጥረት ሁሉ ወንድና ሴት ሆነው ወደ መርከቡ የገቡት እግዚአብሔር እንዳዘዘው ገቡ፤ ጌታም በስተ ኋላው ዘጋበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ሥጋ ካለው ሁሉ የገ​ቡ​ትም ተባ​ትና እን​ስት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኖኅን እን​ዳ​ዘ​ዘው ገቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም መር​ከ​ብ​ዋን በስ​ተ​ውጭ ዘጋት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ሥጋ ካለው ሁሉ የገቡትም ተባትና እንስት እግዚአብሔርም በስተ ኋላው ዘጋበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 7:16
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚህ ዐይነት እስትንፋስ ካላቸው ፍጥረቶች ከእያንዳንዱ ዐይነት ሁለት ሁለት እየሆኑ ከኖኅ ጋር ወደ መርከቡ ገቡ፤


የጥፋት ውሃ አርባ ቀን ድረስ በመዝነብ እየበረታ ሄደ፤ የውሃውም ጥልቀት እየጨመረ ስለ ሄደ መርከቡን ከምድር በላይ ከፍ አደረገው፤


ኖኅም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ።


ጥንድ ወንድና ሴት እየሆኑ፥ እግዚአብሔር ኖኅን ባዘዘውም መሠረት ወደ ኖኅ ወደ መርከቡ ገቡ።


እግዚአብሔር ያፈረሰውን ማንም መልሶ መሥራት አይችልም፤ እግዚአብሔር ያሰረውንም ማንም ሊፈታው አይችልም፤


ስለዚህ ምድር ብትናወጥ፥ ተራራዎች ወደ ጥልቅ ባሕር ቢወድቁ፥


በመንገድህ ያለ ፍርሀት ተማምነህ መሄድ ትችላለህ፤ ከቶም አትሰናከልም።


ሞኞቹ ልጃገረዶች፥ ዘይት ለመግዛት በሄዱበት ወቅት ሙሽራው መጣ። ተዘጋጅተው የነበሩትም ልጃገረዶች ከሙሽራው ጋር ወደ ሠርጉ ግብዣ አዳራሽ ገቡ፤ በሩም ተዘጋ።


የቤቱ ጌታ ተነሥቶ በሩን ይዘጋዋል፤ እናንተም በደጅ ቆማችሁ በሩን በማንኳኳት፥ ‘ጌታ ሆይ! እባክህ ክፈትልን!’ ማለት ትጀምራላችሁ፤ እርሱም ‘ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም!’ ሲል ይመልስላችኋል።


ዘለዓለማዊ አምላክ መጠጊያህ ዘለዓለማዊ ክንዶቹ ደጋፊዎች ናቸው፤ ጠላትን ከፊትህ ያባርራል፤ እንድትደመስሳቸውም ያደርጋል።


እናንተም በመጨረሻው ቀን ለሚገለጠው መዳን በእምነት አማካይነት በእግዚአብሔር ኀይል ተጠብቃችኋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች