Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 7:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የጥፋት ውሃ አርባ ቀን ድረስ በመዝነብ እየበረታ ሄደ፤ የውሃውም ጥልቀት እየጨመረ ስለ ሄደ መርከቡን ከምድር በላይ ከፍ አደረገው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የጥፋት ውሃም ለአርባ ቀናት ያለ ማቋረጥ በምድር ላይ ዘነበ፤ ውሃው እየጨመረ በሄደ መጠን መርከቧን ከምድር ወደ ላይ አነሣት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የጥፋትም ውኃ በምድር ላይ አርባ ቀን አላቋረጠም፥ ውኃውም በዛ፥ መርከቢቱንም አነሣ፥ ከምድርም በላይ ከፍ አለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የጥ​ፋት ውኃ በም​ድር ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ነበረ፤ ውኃ​ውም በዛ፤ መር​ከ​ቢ​ቱ​ንም አነሣ፤ ከም​ድ​ርም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የጥፋትም ውኂ በምድር ላይ አርባ ቀን ነበረ ውኂውም በዛ መርከቢቱንም አነሣ ከምድርም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 7:17
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዝናብም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዘነበ።


ፍጥረት ሁሉ ወንድና ሴት ሆነው ወደ መርከቡ የገቡት እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ነው፤ ከዚህ ቀጥሎ እግዚአብሔር ከኖኅ በስተኋላ የመርከቡን በር ዘጋ።


ውሃ በምድር ላይ እያደገና እየበረታ በሄደ መጠን መርከቡ በውሃው ላይ መንሳፈፍ ጀመረ።


የፈጠርኩትን ሕያው ፍጡር ሁሉ ከምድር ገጽ ላይ ለማጥፋት ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ዝናብ አዘንባለሁ።”


መኖሪያውን በሰማያት ያደረገ፥ ጠፈርን ከምድር በላይ ያጸና፥ የባሕሩን ውሃ አዞ በምድር ላይ እንዲፈስ የሚያደርግ፥ ስሙ እግዚአብሔር ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች